1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ካይሮ፣ ተቃውሞ በፕሬዚዳንት ሙርሲ ላይ፤

ዓርብ፣ ኅዳር 14 2005

ካይሮ መዳረሻ ላይ አንድ የፓርቲው ጽ/ቤት ሊቃጠል ሲል ተግትቷል። በተለያዩ ጠ/ግዛቶች፤ በተቃዋሚዎችና በእስላማውያን አካራሪዎች መካከል ግጭት መፈጠሩ ታውቋል። በካይሮ ታህሪር አደባባይ የተሰበሰቡ ሰልፈኞች፤ ሙርሲ መፈንቅለ መንግሥት ነው ያደረጉት በማለት ዘልፈዋቸዋል።

https://p.dw.com/p/16p3g
Supporters of Egyptian President Mohamed Mursi chant pro-Mursi slogans as they praise a new decree issued on Thursday, during a protest in front of the presidential palace in Cairo November 23 , 2012. Mursi triggered controversy on Thursday by issuing a decree likely to lead to retrials of Hosni Mubarak and his aides but which was compared to the ousted leader's autocratic ways. REUTERS/Asmaa Waguih (EGYPT - Tags: POLITICS CIVIL UNREST)
ምስል Reuters

የግብፅ ፕሬዚዳንት ሙሐመድ ሙርሲ፣ የሥልጣን አካላትን በመላ በማጠቃለል፣ ሥልጣናቸውን ይበልጥ በማጠናቀራቸው፤ ከህዝቡ ዘንድ ብርቱ ተቃውሞ ማስከተሉ ተነገረ። የተቃውሞ ሠልፈኞች፤ የእስላም ወንድማማች ማኅበር የተሰኘውን የፕሬዚዳንቱን ፓርቲ በዛ ያሉ ጽ/ቤቶች፣ በእስክንድሪያ፤ ፖርት ሰዒድና ሱዌዝ ማቃጠላቸው ተገልጿል። ካይሮ መዳረሻ ላይ አንድ የፓርቲው ጽ/ቤት ሊቃጠል ሲል ተግትቷል። በተለያዩ ጠ/ግዛቶች፤ በተቃዋሚዎችና በእስላማውያን አካራሪዎች መካከል ግጭት መፈጠሩ ታውቋል። በካይሮ ታህሪር አደባባይ የተሰበሰቡ ሰልፈኞች፤ ሙርሲ መፈንቅለ መንግሥት ነው ያደረጉት በማለት ዘልፈዋቸዋል። በፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤትና በበሉክሶር ከተማ የሙርሲ ደጋፊዎች አደባባይ በመውጣት ለርእሰ-ብሔሩ ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።ሳሜህ አሹር የተባሉት የተቃውሞው ወገን ፖለቲከኛ እንዲህ ብለዋል።---
«ይህ ሙሉ በሙሉ፤ ሥልጣን ላይ እንዲወጡ ባበቋቸው የአብዮቱ ሚዛናዊ ኃይሎች ላይ የተሠነዘረ ጥቃት ነው። የፕሬዚዳንቱ እርምጃ ፣ ይፋ የመንግሥት የሥልጣን አካላትን በመላ በቁጥጥር ሥር የሚያውል ነው። ይህ ደግሞ ፣ ከሆስኒ ሙባረክ የባሱ አምባገነን እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።»

Supporters of Egyptian President Mohamed Mursi chant pro-Mursi slogans as they praise a new decree he issued on Thursday, during a protest in front of the presidential palace in Cairo November 23 , 2012. Mursi triggered controversy on Thursday by issuing a decree likely to lead to retrials of Hosni Mubarak and his aides but which was compared to the ousted leader's autocratic ways. REUTERS/Asmaa Waguih (EGYPT - Tags: POLITICS CIVIL UNREST)
ምስል Reuters

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ