1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኬንያ ለአፍሪቃ ኅብረት ያቀረበችዉ ኃሳብና የኬንያ መኮንኖች ቅሌት

ሰኞ፣ ጥር 23 2008

የኬንያዉ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሶማልያ ለሰፈረዉ የአፍሪቃ ኅብረት ጦር ጠንካራ ድጋፍና አዲስ የስልጣን ኃላፊነት እንዲሰጠዉ ሲሉ አዲስ አበባ ላይ በተካሄደዉ 26ኛዉ የአፍሪቃ ኅብረት ጉባዔ ላይ ንድፈ ኃሳብ አቀረቡ።

https://p.dw.com/p/1Hn0w
African Union Mission in Somalia
ምስል picture-alliance/dpa/S. Price/Au-Un Ist

[No title]


ፕሬዚዳንቱ ይህን ኃሳብ ያቀረቡት በሶማልያ የኧሸባብ ጽንፈኛ ቡድን ታክቲኩን እየቀያየረ ጥቃት እያደረሰ መሆኑን ተከትሎ እንደሆነ ነዉ የተጠቀሰዉ። በሌላ በኩል በሶማልያ የሰፈረዉ የኬንያ ጦር ባልደረቦች ከኧሸባብ ጋር ግንኙነት እንዳላቸዉና በተለይ ደግሞ ከሰልና ሌሎች ቁሳቁሶችን እንደሚነግዱ በቅርቡ የወጣ አንድ ዘገባ አጋልጦአል። በሶማልያ የሚገኙ የኬንያ የጦር መኮንኖች ቀረጥ ይቀበላሉ ስኳር ይነግዳሉ፤ የሚል ወቀሳም ተያይዞ ይፋ ሆኖዋል። በኬንያ ናይሮቢ የሚገኘዉን የዶይቼ ቬለን ወኪል ፕሬዚዳንት ኡሁሪ ኬንያታ በአፍሪቃ ኅብረት ጉባዔ ላይ አቀረቡት ስለተባለዉ ንድፈ ኃሳብና፤ የኬንያ የጦር መኮንኖችን ቅሌት በተመለከተ በስልክ ጠይቀነዉ ነበር።


ፋሲል ግርማ


አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ