1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኬንያ፣ የምርጫ ውጤት እና ውዝግቡ 

ረቡዕ፣ ነሐሴ 3 2009

በኬንያ ትናንቱ አጠቃላይ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ ተጠናቋል። ዛሬ የፕሬዚደንታዊው ምርጫ  የመጀመሪያ ውጤቶች ከወጡ በኋላ ግን በመዲናይቱ ናይሮቢ እና በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ተቃውሞ እና ሁከት መታየቱን የዜና ምንጮች አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/2hxHm
Kenia nach Wahlen Unruhen und Protest
ምስል Reuters/T. Mukoya

አወዛጋቢ የሆነው የኬንያ ምርጫ

በአስመራጩ ኮሚሽን ድረ ገጽ ላይ እንደተነበበው፣ እስካሁን ከተቆጠረው 92% የመራጭ ድምፅ መካከል ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ 54 ከመቶ በማግኘት እየመሩ ነው። የመራጭ ድምፅ ከሚከማችበት ዋና ኮምፒውተር ድምፅ ተሰርቋል በሚል የኬንይታ ተቀናቃኝ ተቃዋሚው ራይላ ኦዲንጋ ወቀሳ ካሰሙ በኋላ ነው ተቃውሞ የተነሳው።  ስለ ኬንያ ምርጫ እና ስለ ውዝግቡ ናይሮቢ ኬንያ የሚገኙትን የፖለቲካ ተንታኝ ፍቅረማርያም መኮንንን በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ፣ የድምፅ ቆጠራው በወቅቱ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገን ነበር በመጀመሪያ የጠየቅኋቸው።

ፍቅረማርያም መኮንን

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ