1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፕሬዝዳንት ኡሑሩ ኬንያታ ቃለ-መሐላ እንዲፈፅሙ መንገድ ይከፍትላቸዋል

ሰኞ፣ ኅዳር 11 2010

የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ኡሑሩ ኬንያታ የተመረጡበት ድጋሚ ምርጫ ለሶስተኛ ጊዜ ይካሔድ በሚል የቀረቡ አቤቱታዎችን ውድቅ አድርጓል። ውሳኔው በመጪው ኅዳር 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ፕሬዚደንት ኡሑሩ ኬንያታ ቃለ-መሐላ እንዲፈፅሙ ያስችላቸዋል። የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በሁሉም ኬንያውያን ዘንድ እኩል ተቀባይነት አላገኘም።

https://p.dw.com/p/2nxNw
Kenia Nairobi Oberstes Gericht bestätigt Wiederwahl Kenyattas
ምስል Reuters/B. Ratner

የኬንያ ፍርድ ቤት ውሳኔ

ዛሬ ረፋድ ላይ ከኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት የሚስተር አሁሩ ኬንያታ ደጋፊዎች ደስታቸውን ሲገልጹ ነበር፡፡ለእኒህ ወገኖች የደስታ ምክንያት የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በድጋሚ የተደረገውን ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ እንዲሰረዝ የቀረቡ ሁለት አቤቱታዎችን ተመልክቶ በዛሬው ዕለት ያስተላለፈው ውሳኔ ነው፡፡

በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ነሐሴ 8 ቀን 2017 የተደረገውን ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ውጤት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ ካደረገው በኃላ ኬንያ በድጋሚ በጥቅምት 26 .2017 ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ አድርጋለች፡፡ የዋነኛው ተቀናቃኝ ናሽናል ሱፐር አሊያንስ ናሳ ፓርቲ ዕጩ የሆኑት ራይላ ኦዲንጋ ቀድመው እራሳቸውን ባገለሉበት በዚህ ምርጫ ኡሁሩ ኬንያታ 98.2 በመቶ የመራጮችን ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸው ተግልጾ ነበረ፡፡
ብዙም ሳይቆይ ዋዜማውና ማግስቱ በተቃውሞና ግጭት የታጀበው የድጋሚ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ውጤት ተሰርዞ ሌላ ሶስተኛ ዙር ምርጫ እንዲካሄድ ለጠቅላይ ፍርድቤት አቤቱታዎች ገብተዋል፡፡
ሀሩን ምዋዉ የተባሉ የፖለቲካ እና የንግድ ሰው ፣ ኸሌፍ ኻሊፋ የተባሉ ሙስሊሞች ለሰብአዊ መብት የተሰኘ ማህበር ሃላፊ ንጆንጆ ምዋዉ የተባሉ የለውጥ አራማጅ በግልና በጋራ ያቀረቧቸውን ሁለት አቤቱታዎች ሲመለከት የሰነበተው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያለፈውን ምርጫ ውጤት መሰረዝ ይፋ ባደረጉት ቺፍ ጀስቲስ ዴቪድ ማራጋ በኩል ውሳኔውን አሰምቷል፡፡

Kenia Präsident Uhuru Kenyatta
ምስል Reuters/B. Ratner

‹‹ፍርድ ቤቱ በሙሉ ድምጽ የቀረቡት አቤቱታዎች ተቀባይነት እንደሌላቸው ወስኗል፡፡እናም የመጨረሻ ትእዛዛችን ጆን ሐሩን ማዉበነጻው የምርጫ እና ወሰን ኮሚሽን ላይ አቅርበውት የነበረው አቤቱታ እንዲሁም ሌሎች ሁለት በጋራ የቀረቡ አቤቱታዎች  በዚህ መሰረት ውድቅ እንዲሆኑ ነው ፡፡ንጆንጆ ሞይ እንዲሁም ሌላ በነጻው የምርጫ ወሰን ኮሚሽን ሊቀመንበር ላይ ያቀረቡት አቤቱታ የሎሎች ሶስት በጋራ የቀረቡ አቤቱታዎም በተመሳሳይ ውድቅ  ተደርገዋል፡፡በዚህም  መሰረት በጎረጎሳዊያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 26 የተደረገው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ አሁሩ ኬንያ ያሸነፉበት ምርጫ ተደርጎ ጸድቋል፡፡›› ብለዋል፡፡
የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተከትሎ ተቃራኒ ስሜቶች ተስተናግደዋል፡፡ኤልዶሬት፣ጋቱንዱ እና ኒሬን በመሰሉ የሚ/ር ኬንያታ ደጋፊ ቦታዎች ነዋሪዎች ደስታቸውን ሲገልጹ የሚያሳዩ ምስሎች በሀገረቱ ቴሉቭዥኖች ላይ ታይቷል፡፡

Kenia Oppositionsführer Raila Odinga
ምስል Getty Images/AFP/Y. Chiba

በአንጻሩ ሞምባሳ እና ኪስሙን በመሰሉ ለሚ/ር ራይላ ኦዲንጋ ድግፍ ሲሰጡ የነበሩ ቦታዎች ዜጎች ማዘናቸውን እና ተስፋ መቁረጣቸውን ሲገልጹ ታይተዋል-በተለይ ቢስሙ ወጣቶች ያገለገሉ የመኪና ጎማዎችን በእሳት ሲለከሱ ታይቷል ፡፡

የተቃዋሚው ናሽናል ሱፐር አሊያንስ መሪ ራይላ ኦዲንጋ የዛሬው የጠቅላ ፍርድ ቤት ውሳኔ ከተሰማ በኃላ በፓርቲያቸው የቲዊተር ገጽ ላይ የውክልና የጽሁፍ መግለጫ አጋርተዋል፡፡በመግለጫው ላይ የፍርድ ቤቱ ውሳኔን በጫና የተገኘ ያሉት ሲሆን ውሳኔው ምንም ምንም ይሁን የአሁኑ መንግስት የህግ መሰረት የለውም ዕውቅናም አንሰጠውም ብለዋል፡፡ ፍርድ ቤቱን አናወግዝም አብረን እናዝንለታለን እንጂ ብለዋል፡፡

ሀብታሙ ስዩም
እሸቴ በቀለ
አርያም ተክሌ