1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ክርክር በኢትዮጽያ የትምህርት ስርአት ላይ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 21 2002

በኢትዮጽያ ፖለቲካ ዉስጥ ለረጅም ግዜ የመከራከርያ ርእስ ሆኖ በቆየዉ በወቅቱ ባለዉ የትምህርት ስርአት ዙርያ በሳምንቱ መጨረሻ በፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር ተካሂዶአል።

https://p.dw.com/p/MhmD

በዚህ ክርክር የገዥዉ ፓርቲ ኢሃዲግ በአንደኛና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ብሎም በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለትምህርት መስፋፋት ባደረገዉ ጥረት አመርቂ ዉጤት ማስመዝገቡን ሲገልጽ ተቃዋሚዎች በበኩላቸዉ የትምህርት መስፋፋቱ የሚገለጽበት አሃዝ መመርመር አለበት ጥራትን መሰረት ያላደረገዉ የትምህርት መስፋፋትም ትዉልድ ገዳይ ነዉ ፣የትምህርት ጥራቱ መበላሸት ለአሁኑ ብቻ ሳይሆን ለወደፊት ሊቃና በማይችልበት ደረጃ ወድቆአል ሲሉ መከራከራቸዉ ተገልጾአል ዝርዝሩን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ልኮልናል።

ታደሰ እንግዳዉ፣ አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ