1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት ይቅርታ ለማን እና እንዴት ይደረጋል?

ማክሰኞ፣ የካቲት 6 2010

የኢትዮጵያ መንግሥት ተጠርጣሪዎችን ክሳቸውን በማቋረጥ ፍርደኞችን ደግሞ በይቅርታ እና በምኅረት ለመልቀቅ ወስኖ እርምጃ ጀምሯል። ክሳቸው ይቋረጣል፣ ይቅርታ ወይም ምሕረት ይደረግላቸዋል ከተባሉ ኢትዮጵያውያን ግን ብዙዎቹ ከእስር አልተለቀቁም።

https://p.dw.com/p/2sdYI
PK von Äthiopiens Generalstaatsanwalt
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

የባለሙያ ማብራሪያ በይቅርታና ምኅረት ጉዳይ

የኢትዮጵያ መንግሥት በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞችን ክስ ለማቋረጥ፣ የተበየነባቸውን ደግሞ በይቅርታ ለመፍታት መወሰኑ አይዘነጋም። የቀረበባቸው ክስ ከተቋረጠላቸው መካከል ዛሬ ከእስር የተፈቱት አቶ በቀለ ገርባ እና ስድስት የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ አመራሮች እና አባላት ይገኙበታል። የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የይቅርታ ሰነድ እንዲፈርሙ ተጠይቀው ሳይቀበሉት ቀርተዋል። የኮሚቴው አራት አባላት ዛሬም ከእስር አልተፈቱም።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና  ፖለቲከኛው አቶ አንዱዓለም አራጌ ጥፋተኛ ተብለው በእስር ላይ ናቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት እስክንድር እና አንዱዓለምን ከሚፈታቸው መካከል እንደሆኑ ቢጠቅስም እስከዛሬ አልተፈቱም። ቤተሰቦቻቸው በኢትዮጵያ መንግሥት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው የግንቦት ሰባት አባል ነበርን የሚል ደብዳቤ እንዲፈርሙ መጠየቃቸውን ተናግረዋል። ክስ ማቋረጥ እና ይቅርታ በኢትዮጵያ ሕግ ያላቸው ልዩነታቸው ምንድነው? የሕግ ባለሙያው አቶ ተማም አባቡልጉ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እሸቴ በቀለ

ሸዋዬ ለገሠ