1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኮትዲቯር ከባግቦ መማረክ በኋላ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 3 2004

በኮት ዲቯር ከህዳሩ 2010 ዓም ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በኋላ የተነሳው ደም አፋሳሽ የመንግሥት ቀውስ ያበቃው ከአንድ ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ነበር። የያኔው ግጭት የተቀሰቀሰው በምርጫው የተፎካከሩት የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ሎውሮን ባግቦ የተፎካካሪያቸውን አላሳ ዋታራ ድል አልቀበል ባሉበትና ሥልጣኑን ዓለም አቀፍ

https://p.dw.com/p/14bnb
epa03025144 Former Ivorian president Laurent Gbagbo appears before the International Criminal Court (ICC) for the first time for his role in the deadly aftermath of presidential polls in November 2010, in the Hague, the Netherlands, 05 December 2011. Gbagbo is accused of of crimes against humanity, including murder and rape, in the aftermath of Ivory Coast's disputed presidential elections in November 2010. Around 3,000 were killed following Gbagbo's refusal to accept defeat in the election polls. EPA/PETER DE JONG / POOL
Elfenbeinküste Laurent Gbagboምስል picture-alliance/dpa

ዕውቅና ላገኙት ዋታራ አላስረክብም በማለት ትግል በጀመሩበት ጊዜ ነበር። በሁለቱ ተቀናቃኝ ወገኖች መካከል ውጊያው ለብዙ ወራት ከቀጠለ በኋላ ባግቦ እአአ ሚያዝያ 11፡ 2010 ዓም በተያዙበት ጊዜ ውዝግቡ ሊያበቃ ችሎዋል። ይሁንና፡ የዶይቸ ቬለዋ ዘጋቢ ካትሪን ጌንስለር እንደታዘበችው፡ ዛሬ ከአንድ ዓመት ሰላም በኋላም ኮት ዲቯር ወደነበረችበት አልተመለሰችም። አርያም ተክሌ

የዋታራ ደጋፊዎች ከፈረንሣይና ከተመድ ዓለም አቀፍ ርዳታ ካገኙ በኋላ ግባግቦን በምሽጋቸው መያዙ ተሳክቶላቸዋል። ይህ ባግቦ የተያዙበት ሁኔታ በዓለም አቀፍ ቴሌቪዥን የታየበት ድርጊት ግን ብዙዎቹን የባግቦ ደጋፊዎች ቅር እንዳሰኘ ነዋሪነቱ በዱዋኬ ከተማ የሆኑት ልብስ ሰፊነት ይተዳደሩ የነበሩት ሮማሪች ጊያዚ የተባሉ መራጭ ዛሬ በሀፍረት ይናገራሉ።
« እኔ ባግቦን ነበር የመረጥኩት። »
ባግቦ መታሰራቸው ከተረጋገጠ በኋላ የዋታራ ጦር በብዛት የባግቦ ደጋፊዎች የነበሩባትን ዱዋኬን ለመቆጣጠር ጥቃት ባካሄዱበት ጊዜ ከከተማይቱ ነዋሪዎች መካከል 30.000 የሚሆኑት ሸሽተው ባካባቢው በሚገኘው የካቶሊካውያን ሰፈር ከለላ መሻቱን የሚስዮኑ ኃላፊ ቄስ ሲፕሪየን አስታውሰዋል።
« ባለፈው ዓመት እአአ መጋቢት ሀያ ስምንት እና ሀያ ዘጠኝ ቀን የታየው ሁኔታ የለየለት ዘግናኝ እና አስፈሪ ነበር። እና ይህ አስከፊ ትዝታ ዛሬም ገና አልተለየንም። »
ይህ ከሆነ ከጥቂት ቀናት በኋላ በመቶ የሚቆጠሩ አስከሬኖች የተጣሉበት የመጀመሪያው ጉድጓድ መገኘቱ ይታወሳል። ከዋታራ ወታደሮች ጥቃት በሕይወት የተረፉት ሁሉ ሁኔታዎች ተረጋግተው ወደመኖሪያ ቦታቸው መመለስ እስከቻሉበት ጊዜ ድረስ የርዳታ ድርጅቶች ተገን ባገኙበት የሚስዮናውያኑ ሰፈር አቅራቢያ በሰሩላቸው ጊዚያዊ መጠለያ ቦታ መቆየት ችለዋል። ደህና ሁኔታ ያጋጥመናል በሚል ወደ ትውልድ ሰፈራቸው ከተመለሱት መካከል በዱዋኬ ከተማ አቅራቢያ ወደለው የፌንጎሎ መንደሩ የተመለሰው ሮዲ ቴሃንዚን ይገኝበታል።
« ጦርነቱ ካበቃ ወዲህ በሀገሪቱ ሁኔታው ተረጋግቶዋል። ሰዉ እንደገና ወደየዕለታዊ ተግባሩ መመለስ ችሎዋል። ይሁንና፡ ሁኔታዎች እንደ ቀድሞ አይደሉም። »
በኮት ዲቯር ሁኔታዎች ወደነበሩበት ላልተመለሱበት ድርጊት የፖለቲካ ታዛቢዎች በዱዋኬ ስለተፈፀመው ወደ ሰላሳ ሺህ ሕዝብ ሕይወቱን ስላጣበት እና ሀምሳ ሺዎችም ስለተፈናቀሉበት ዘግናኝ ድርጊት ሀቁን ለማሳወቅና ተጠያቂዎቹን ለፍርድ ለማቅረብ አለመሞከሩን እንደምክንያት ጠቅሰዋል። እርግጥ አላሳን ዋታራ በደቡብ አፍሪቃ ከአፓርታይድ ሥርዓት ከተገረሰሰ በኋላ የተቋቋመውን ዓይነት የሀቅ አፈላላጊና ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን እአአ መስከረም 2011 ዓም ቢያቋቁሙም፡ ኮሚሽኑ በይፋ ሥነ ሥርዓት ከተቋቋመ ወዲህ ስለስራው የተሰማ ነገር የለም። ኮሚሽኑ ለዱዋኬ ዕልቂት ተጠያቂዎቹን ለፍርድ ማቅረብ ይቅርና ዕልቂቱ ስለመካሄዱ እንኳን እስከዛሬ አንዳችም ምርመራ አለማድረጉን የከተማይቱ ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ሂውማን ራይትስ ዎችም አጥብቆ ነቅፎዋል። እንደ ሂውማን ራይትስ ዎች አስተያየት፡ ሥልጣን በተረከቡበት ጊዜ ራሳቸውን ኃላፊነት የሚሰማቸው መሪ አድርገው ያቀረቡት ዋታራ ከላይቤሪያ ጋ በሚያዋስነው ከመዲናይቱ ራቅ ብሎ በሚገኘው የሀገራቸው አካባቢ ስላለው ሁኔታ ደንታ የላቸውም።

Wer hat das Bild gemacht/Fotograf?: Katrin Gänsler Wann wurde das Bild gemacht?: 26. Oktober 2011 Wo wurde das Bild aufgenommen?: Duékoué, Elfenbeinküste eingereicht am 11.4.2012 von Katrin Gänsler Freie Journalistin in Westafrika/Freelance journalist in West Africa
የዱዋኬ መጠለያ ጣቢያምስል DW
Ivory Coast President Alassane Ouattara poses on the TV set of French channel TF1 prior to an interview that was part of the evening news broadcast, Tuesday Sept. 13, 2011 in Paris. (AP Photo/Fred Dufour, Pool)
ፕሬዚደንት አላሳ ዋታራምስል AP

ካትሪን ጌንስለር/አርያም ተክሌ
ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ