1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኮፐንሃገን ወይስ ካንኩን?

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 5 2003

የዓለም የሙቀት መጠን መጨመሩም ሆነ የአየር ንብረት ለዉጥ በየስፍራዉ በሚያስከትለዉ መዘዝ ገሃድ የሆነ ክስተት መሆኑ ሁሉንም ያግባባል።

https://p.dw.com/p/QY2f
በደኖች አማካኝነት በካይ ጋዞችን መቀነስን የተቃወሙ ሰልፈኞች በካንኩንምስል DW

ጉዳዩን በቅርበት እያጠኑ መረጃዎችን ይፋ የሚያደርጉ ወገኖች የፖለቲከኞቹን ቀልብ ያገኙት እንዲህ በዋዛ አልነበረም። ልፋታቸዉ ትኩረትን ሳበናም በተመድ አማካኝነት ጃፓን ቶኪዮ ላይ የተሰባሰቡት አባል አገራት ከግዙፍ እንዱስትሪዎቻቸዉ ወደከባቢ አየር በሚለቀቁ በካይ ጋዞች መዘዝ የሚመጣዉን ተፈጥሯዊ ኡደት መዛባት በሰዉ ሰዉኛዉ ለማረም ወደ40 የሚጠጉ የበለጸጉ አገራት የሚለቁትን የበካይ ጋዞች መጠን በስምምነት አስፍረዉ ሊተገብሩ የኪዮቶን ዉል ተፈራረሙ። ይህ ስምምነት የሚያከትምበት ጊዜ እየቀረበ በሄደ መጠን ግን ከተሰራዉ የተረፈዉ ስለበረከተ፤ የተጠቀሰዉ የአየር ንብረት ለዉጥም የጎሉ ክስተቶችን ማስመዝገቡን ሲደጋግም እሱን የሚተካ ስምምነት እንደሚያስፈልግ ታመነበትና በ194 የመንግስታቱ ድርጅት አባል አገራት መካከል ድርድሩ ተጀመረና ከባሊ፤ ለኮፐንሃገን ብሎም ለካንኩን ዉሎች በየፍርጅ ፈርጁ እየተቋጠሩ ይወርዱ ያዙ። ብዙ ታቅዶለት፤ ብዙ ተብሎለት፤ ብዙም ተጠብቆበት በመጨረሻ የቀዘቀዘዉን የኮፐንሃገኑን ጉባኤ የተመለከቱ ወገኖች ስለካንኩን ብዙም ሳያወሩ፤ እጅግም ተስፋ ሳይሰጡም ሆነ ሳይነሱ ቀኑ ደረሰና ጉባኤ ተካሂዶ፤ ካንኩንም በተራዉ ለደርባኑ ጉባኤ መስመር አበጅቶ ተጠናቀቀ።

ሸዋዬ ለገሠ ሂሩት መለሰ