1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወሲባዊ ጥቃት በኢትዮጵያ

እሑድ፣ ኅዳር 21 2007

በኢትዮጵያ የሚፈጸመውን ወሲባዊ ጥቃት አሳሳቢ ነው ተባለ። በ17 ዓመቷ ታዳጊ ሐና ላላንጎ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሞባት ህይወቷ ካለፈ በኋላ ድርጊቱ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል።

https://p.dw.com/p/1Dx3g
Symbolbild Häusliche Gewalt
ምስል picture-alliance/dpa

የ10ኛ ክፍል ተማሪ እና የ17 ዓመት ታዳጊ ነበረች። አዲስ አበባ ውስጥ ከአየር ጤና ወደ ጦር ኃይሎች ልትጓዝ በተሳፈረችበት ሚኒባስ ታክሲ ውስጥ በነበሩ አምስት ሰዎች ታፍና ተወስዳ በተደጋጋሚ በመደፈሯ ለሞት የተዳረገችው-ሐና ላላንጎ። ታዳጊዋን አፍነው በመውሰድ ደፍረዋል በሚል የተጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው በምርመራ ላይ ናቸው። በሐና ላላንጎ ላይ የተፈጸመው ወሲባዊ ጥቃት በመገናኛ ብዙሃን ይፋ ከሆነ በኋላ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል።

ፌስቡክን በመሳሰሉ ማህበራዊ ድረ ገጾች ኢትዮጵያያን ፎቶ ግራፏን በመለጠፍ እና 'ፍትህ ለ ሐና' የሚሉ ሃሳቦችን በማስተጋባት ቁጣቸውን ገልጸዋል።በዚህ ሳምንት የዶይቸ ቬለ የውይይት መድረክ ወሲባዊ ጥቃት በኢትዮጵያ ያለውን ገጽታ እንፈትሻለን።

እሸቴ በቀለ

ልደት አበበ