1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወታደራዊው ጁንታና ውጥረት በጊኒ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 17 2001

የጊኒ የቀድሞ ባለስልጣናት የተሰጣቸዉ የ24 ሰዓት የጊዜ ገደብ ሳያልቅ ስልጣን ከተቆናጠጠዉ ወታደራዊ ጁንታ ጋ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸዉን ገለጹ።

https://p.dw.com/p/GNYY
የላንሳና ኮንቴ ስንብት
የላንሳና ኮንቴ ስንብትምስል AP

ጊኒን ለሃያ አራት አመታት በአምባገነንነት ሲገዟት ቆይተው ባለፈው ሰኞ ያረፉት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ላንሳ ኮንቴ ዜና ረፍትን ተከትሎ ወታደራዊ ጁንታ የአመራሩን ቁንጮ መቆጣጠሩን ገልፆ እንደነበር ይታወቃል። የቀድሞ የመንግስት ባለ ስልጣናት ዛሬ ዋና ከተማዋ ኮናክሬ ተገኝተው የጁንታው መሪ ሻለቃ ሞሳ ዳዲስ ካማራን ፕሬዚዳንት ማለታቸውም ታውቓል።