1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀዉስ

ዓርብ፣ ጥቅምት 4 2009

ኢትዮጵያ ወደ አዘቅት እየተንደረደረች በመሆንዋ የጉዳዩን አሳሳቢነት መንግሥት ሊያጤነዉ እንደሚገባ  የዶይቼ ቬለዉ ሉድገር ሻዶምስኪ ዛሬ በጀርመንኛ ይፋ ባደረገዉ ኃተታዉ አሳስቦአል።

https://p.dw.com/p/2RFga
Infografik Karte Proteste und Ausschreitungen in Äthiopien 2016

Ber.Berlin (Kommentar-Beka 2.0- das Vorzeigeland Äthiopien versinkt im Chaos) - MP3-Stereo

  
የኢትዮጵያ ሁኔታ የተዛባ ይመስላል ሲል የሚጀምረዉ የዶቼ ቬለዉ ጋዜጠኛ በኃተታዉ በሀገሪቱ ለብዙ ዘመናት ታምቆ የነበረዉ የሕዝቦች አለመግባባት የፀጥታ ኃይላት በሚወስዱት የጥቃት ርምጃ ችግሮች እየተባባሱ ነገሩ ከቁጥጥር ዉጭ በመዉጣት ላይ እንደሚገኝ ይጠቁማል። የኦሮሞ እና የአማራ ብሔረሰቦች መብታችን ይከበር ብለዉ መነሳታቸዉ፤ ወጣቱ ትዉልድ በበኩሉ ሥራና የሚበላ ዳቦን እፈልጋለሁ ብሎ በአንድነት መቆሙ፤ በሀገሪቱ ከልክ ያለፈ በስልጣን መባለግ በግልፅ መኖሩን ያመለክታል ይላል ጽሑፉ። መንግሥት በሀገሪቱ ለተቀሰቀሰዉ ተቃዉሞ በዉጭ ኃይላት ላይ ከማላከክ ይልቅ የጣለዉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንስቶ በሥራ ላይ እተረጉመዋለሁ ያለዉን ተሐድሶ ገቢራዊ ማድረግ ይገባዋል። የቆለፈዉን የመገናኛ ብዙኃን ዘዴዎችን መክፈት ይኖርበታል ሲል ጋዜጠኛዉ በኃተታዉ ዘርዝሮአል። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል፤ የሉድገር ሻዶምስኪን ኃተታ ተርጉሞ ልኮልናል።

    
ይልማ ኅይለሚካኤል / ሉድገር ሻዶምስኪ 
ነጋሽ መሐመድ 
አዜብ ታደሰ