1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወደ ትዉልድ ሃገሩ የተመለሰዉ ሶርያዊዉ ስደተኛ

ማክሰኞ፣ የካቲት 1 2008

በዓለም ስላለዉ የስደተኞች ቀዉስ በተለይ ደግሞ ወደ ጀርመን ስሚተመዉ የተገን ጠያቂ ብዛትና በጀርመን ስለሚኖሩ ስደተኞች ጉዳይ ብዙ ተነግሮአል። እንዲያም ሆኖ ተገን ለመጠየቅ ወደ ጀርመን ገብተዉ በሀገሪቱ ሁኔታዉ ስላልተመቻቸዉ ወደ ትዉልድ ሀገራቸዉ ስለሚመለሱ ስደተኞች ብዙም የተነገረ ነገር የለም።

https://p.dw.com/p/1Hs38
Wissam Faraschi
ምስል WDR

[No title]


ሥራ አለመሥራት በራሱ ጭንቅላት ያደንዛል ይላል ጀርመን ዉስጥ በስደተኝነት የኖረዉ የ38 ዓመቱ ሶርያዊ ቫሲም ፋራሺ። ቫሲም እዚህ ጀርመን ለ 20 ወራቶች ማለት ወደ ሁለት ዓመት ግድም ተቀምጧል። አብዛኛዉን ይህን ጊዜዉን ያሳለፈዉ ደግሞ በምሥራቃዊ ዌስት ፋልያ ግዛት ሆፍልሆፍ በምትባል አነስተኛ ከተማ ዉስጥ ነዉ። ቫሲም በጀርመን ሆፍልሆፍ ከተማ በቆየባቸዉ ጊዜያት እጅግ ይመኘዉ የነበረዉን ሥራ ማግኘት ግን አልቻለም። ሶርያ ሳለ በግሉ የምህንድስና ሥራ ይሠራ እንደነበር የሚናገረዉ ቫሲም በስደት ዓለም ጀርመን ዉስጥ ማንኛዉንም ዓይነት ሥራ ቢያገኝ ወደኋላ አይልም ነበር።

Flüchtlingsunterkunft in Würzburg
ምስል DW/N. Jolkver

« ሥራን ለማግኘት ወደ ሥራ ሚኒስቴር፤ እንዲሁም የሥራ አፈላላጊ ማዕከል ወደተባሉት ቦታዎች ሁሉ ሄጃለሁ። ምንም ዓይነት እድልን ግን አላገኘሁም። አሉ የተባሉትን የምግብ ቤቶች፤ ፋብሪካዎችና የግንባታ ሥራ ተቋማትን ሁሉ ጠይቄያለሁ። በግድ በምህንድስና ሥራ መሰማራት የለብኝም። ግን የሆነ ነገር መሥራት ይኖርብኛል። አንድ ዓመት ከአስር ወር ያለሥራ መቀመጥ፤ ጭንቅላትን ያደንዛል፤ታምሜያለሁ።»


ቫሲም ፋራሺ፤ ጀርመን ሆፍልሆፍ ከተማ ሳለ እንደተረሳ ዜጋ ነበር ራሱን ይቆጥር የነበረዉ። ጀርመን ደርሶ በዚች አነስተኛ ከተማ የመኖርያ ፈቃድ ተሰጥቶ ከዚያም ሥራ መሥራት የሚያስችል ፈቃድን እስኪያገኝ ድረስ የጠበቀዉ በጣም ብዙ ጊዜ እንደነበርም ቫሲል ይናገራል። የኖረዉም ከጀርመኖች ተቀላቅሎ ሳይሆን ከሌሎች ሃገራት ከመጡ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ነበር።
«እዚህ ያለሁት ብቻዬን ነዉ። ጓደኛም ሆነ ባልደረባ የምለዉ ጀርመናዊ የለም። ሥራ ለማግኘት ጥሩ ሰዎችን መተዋወቅ ይኖርብኛል። ግን እኔ ሊረዳኝ የሚፈልግ ሰዉ እንኳ አላየሁም። አንድም ሰዉ አላገኘሁም። »

Wissam Faraschi
ሥራ አለመሥራት በራሱ ጭንቅላት ያደንዛል-ቫሲም ፋራሺምስል WDR


ቫሲም በሚኖርባት በትንሽዋ ሆፍልሆፍ ከተማ ስደተኞችን የሚረዱ በርካታ ነዋሪዎች አሉ። እነዚህ ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ አብዛኞቹ ስደተኞች ሥራ ስለሌላቸዉ ደስተኞች አይደሉም፤ በዚያ ምክንያት አብዛኞቹ አልኮል መጠጥ ይጠጣሉ፤ አንዳዶቹም መጫወት ይጀምራሉ። ቫሲም በበኩሉ ጀርመናዉያን «የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ባህል» የሚሉትን ሁሉ ይተቻል።
«እኛ ወዳለንበት የሚመጡ ተገን ጠያቂዎች ሁሉ ጀርመን «ገነት ናት» ብለዉ ነዉ የሚያስቡት። ስደተኞቹ ጀርመናዉያን ትንሽም ቢሆን ይረዳሉ ብለዉ ያስባሉ። ይህ ግን ሃሰት ነዉ። ሁሉ ነገር ዉሸት ,,ዉሸት ,,ዉሸት»


ቫሲም ፋራሺ በጀርመን ከሁለት ዓመት ግድም ቆይታ በኋላ ወደ ሃገሩ ለመመለስ ሲዘጋጅ በሻንጣ እንኳ የሚይዘዉ አንድም እቃ አልነበረዉም። እቃ ይዟል ቢባል የለበሰዉ ልብስ ፤ መንገድ ላይ የሚቆረጥመዉ አንድ ሁለት ብስኩትና እሱነቱን የሚገልፁ መረጃ ወረቀቶች እንዲሁም የሚቀበሉት ቤተሰቦቹ ወደ አሉበት ወደ ሊባኖስ የሚመልሰዉ የአዉሮፕላን ቲኬት ብቻ ነዉ። « አሁን ጉዞዉ ወደ ፍራንክፈርት ነዉ። ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ዓለም አቀፉ የአየር ጣብያ ወደሚገኝበት ወደ ፍራንክፈርት። ከዚያ ወደ ኢስታንቡል። ከኢስታንቡል ወደ ቤይሩት። ጀርመን አመሰግናለሁ። ግን ይህን የሁለት ዓመት ትዝታዬን ከጭንቅላቴ እሰርዛለሁ። »

Auf dem Weg nach Deutschland oder Schweden Flüchtlinge in Kroatien
ምስል DW/Z. Ljubas


ቫሲም ጀርመን ዉስጥ በስደተኝነት የቆየበትን ጊዜ ትዉስታዉን ከአዕምሮዉ ለመፋቅ የሚችል ላጲስ ቢኖር ምኞቱ ነበር። እስከ ወድያኛዉ ላለማስታወስ። ቫሲም ይህን የተናገረዉ ፍራንክፈርት ወደሚገኘዉ ዓለም ዓቀፍ አዉሮፕላን ጣብያ ለመሄድ የረጅም ርቀት አዉቶቡስን ሲሳፈር ነበር። እንደ ቫሲም፤ በርስ በርስ ጦርነት በምትናጠዉ በሶርያዋ ትንሽዋ የትዉልድ መንደሩም ቢሆን ከዚህ የባሰ የከፍ ነገር አያጋጥመዉም,,,


ቶማስ ቮስተማን / አዜብ ታደሰ


ሸዋዬ ለገሠ