1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዊኪ ሊክስና የዓለም ዲፕሎማሲ

ሰኞ፣ ኅዳር 27 2003

የአዉሮጳ አሜሪካኖችን አንድነት ሸርሽሮ-ልዩነታቸዉን፣ የአረብ-እስራኤሎችን የጠላትነት መጋረጃ በርቅሶ ተቀራራቢነታቸዉን አፈጋዉ።ዊኪ ሊክስና-ዘገባዉ።

https://p.dw.com/p/QQtE
የዊኪሊክስ መስራች-ጁሊያን አሳንጅምስል AP

ቃዛፊን እና ኔታንያሁን ከጠላትነታቸዉ እኩል-እኩል አስደሰታቸዉ።የቤጂንግና የፒዮንግዮንግን የወዳጅነት ሰንሰለት ፈርቅቆ በተቃርኖ አቆማቸዉ።የአሕመዲንጃድን እና የፑቲንን የቋንቋ-የአቅም ርቀትን ጥሶ ባንድ አገላለፅ-አንድ አደረጋቸዉ።የሳራ ፔለንንና የሒላሪ ክሊንተንን ልዩነት ጥሶ-ባንድ አሳደማቸዉ።የአዉሮጳ አሜሪካኖችን አንድነት ሸርሽሮ-ልዩነታቸዉን፣ የአረብ-እስራኤሎችን የጠላትነት መጋረጃ በርቅሶ ተቀራራቢነታቸዉን አፈጋዉ።ዊኪ ሊክስና-ዘገባዉ።ከሁሉም በላይ ዓለም-ኑሮ ሕይወቱን ሥለሚበይኑት መሪዎቹ የነበረዉን አለመለካከት ለወጠዉ።እንዴት-ለምን? የጂዳ፣ የበርሊን፥ የዋሽንግተን ዘጋቢዎቻችን አብረዉኝ አሉ-ላፍታ አብረን እንጠይቅ።

ነቢዩ ሲራክ

ይልማ ሐ/ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ