1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የሞስኮ ጉብኝት

ሰኞ፣ ሰኔ 19 2009

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ዛሬ በሞስኮ ከሩስያ አቻቸው ሴርጌይ ላቭሮቭ ጋር ተወያዩ። ሁለቱ ባለስልጣናት ከመከሩባቸው የተለያዩ ዘርፎች መካከል ሽብርተኝነትን መዋጋት አንዱ እንደነበር ዶክተር ወርቅነህ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።  

https://p.dw.com/p/2fQoc
Russland Moskau Außenminister Lawrow und Amtskollege Gebeyehu Äthiopien
ምስል Getty Images/AFP/N. Kolesnikova


«ሽብርተኝነት በርግጥ ለአፍሪቃ ትልቅ ችግር ነዉ። ይህ ችግር በአፍሪቃ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታይ ነዉ። በተለይ ደግሞ በአፍሪቃዉ ቀንድ። በሶማልያ ኧሸባብ የደቀነዉን ሽብርተኝነት እየተዋጋን ነዉ። እንደምታዉቁት  ኢትዮጵያ  በአፍሪቃ ሰላምን ለማስፈኑ ከፍተኛ አስተዋችኦ እያደረገች ናት። በሶማልያ ኧሸባብን እንዋጋለን፤ በአጠቃላይ ሽብርተኝነትን በአፍሪቃ ኅብረት ስር ባንድነት በመዋጋት ላይ እንገኛለን።»      
የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በፀረ ሽብሩ ትግል ላይ ኢትዮጵያ እና አፍሪቃ የሩስያ ድጋፍ እንደማይለያቸው ገልጸዋል።
« ሽብርተኝነትን ከሚዋጉት አፍሪቃዉያን ሃገራት ጋር ትብብራችንን እናረጋግጣለን። የሽብርተኝነት ስጋት የተፈጠረው የቀጠናዉ አባል ሃገራት ያልሆኑ፤ ምዕራባዉያት ሃገራት ባካባቢው የማይመቿቸውን መንግሥታት ዓለም አቀፍ ሕግን በመጣስ ለማውረድ የተለያዩ ፕሮዤዎችን ይዘው በተንቀሳቀሱበት ጊዜ ነው። »
የሩስያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ፤  በጎርጎረሳዊዉ 2014 ዓ.ም የአዲስ አበባ ጉብኝታቸዉን በጥሩ እንደሚያስታዉሱ ገልፀዋል።  የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ባለፈዉ ዓመት ሩስያን መጎብኘታቸዉ የሚታወስ ነው።
 

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ