1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ቀን

ዓርብ፣ ሚያዝያ 23 2007

ዓለም ዓቀፉ የሠራተኞች ቀን በዓለም ዙሪያ የሠራተኛ ማህበራት ባካሄዷቸው የአደባባይ ሰልፎች ዛሬ ተከብሮ ውሏል። በጀርመን የተለያዩ ከተሞች በተካሄዱ ሰልፎች የሠራተኛው ጥያቄዎች መልስ እንዲሰጣቸው ጥሪ ቀርቧል።

https://p.dw.com/p/1FIri
Tag der Arbeit Deutschland Maikundgebung in Berlin Demo
ምስል picture-alliance/dpa/W. Kumm



ኩባንያዎች ከጀርመን ውጭ በአነስተኛ ክፍያ የሚያካሂዱት ብዝበዛ እንዲቆምም ተጠይቋል። ከሌሎች ዓመታት ጋር ሲነፃጸር ዘንድሮ በርሊንን ጨምሮ በአውሮፓ ታላላቅ ከተሞች ከተካሄዱት ሰልፎች አብዛኛዎቹ ሰላማዊ ነበሩ። በጀርመን መዲና በርሊን ላይ የጀርመን የሠራተኛ ማኅበር ቀኑን በማሰብ ባካሄደዉ ሰላማዊ ሰልፍ በያዝነዉ የጎርጎረሳዊ ዓመት መጀመርያ ሥራ ላይ የዋለዉ የዝቅተኛ ደመሞዝ መጠን እንዳይቀለበስ ሲል ጥሪዉን አቅርቧል።

የጀርመን የሠራተኛ ማኅበር ሊቀመንበር ራይነር ሆፍማን በሰልፉ ላይ ባደረጉት ንግግር ለ «ዝቅተኛ የደመሞዝ መጠን» የወጣዉ ሕግ ፀንቶ መቀጠል እንደሚኖርበት አሳስበዋል። ሕጉ በመዋለ ንዋይ አፍሳሾችና፤ በክርስትያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ ና በእህት ፓርቲዉ በክርስትያን ሶሻል ፓርቲ CDU/CSU እንዳይሻይር መጠበቅ አለብን ሲሉም አስገንዝበዋል። እዚሁ በጀርመን በቫይመር ከተማ የተካሄደዉ የዉይይት መድረክ እና ዝግጅት ደግሞ፤ በቀኝ አክራሪዎች ጥቃት ደርሶበታል ።

Tag der Arbeit Deutschland Maikundgebung in Berlin DGB Chef Hoffmann
የጀርመን የሠራተኛ ማኅበር ሊቀመንበር ራይነር ሆፍማንምስል Getty Images/C. Koall

በዉይይት ሥነ-ስርዓቱ ላይ የሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ አባል ንግግር አድራጊ ላይ ጥቃት እንደተጣለ ነዉ የተመለከተዉ። በጥቃቱ ቢያንስ 15 ሰዎች እንደተጎዱ ነዉ የተጠቀሰዉ። ሆኖም ቱርክ ውስጥ ሰልፈኞች ከፀጥታ ኃይሎች ጋር መጋጨታቸው ተዘግቧል። ኢስታንቡል ታክሲም አደባባይ ተሰብስቦ የነበረዉን ሰልፈኛ ለመበተን ፖሊስ አስለቃሽ ጢስና ዉኃን ረጭቶአል። ከ130 በላይ ሰልፈኞች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸዉም ተዘግቦአል።


ይልማኃይለ ሚካኤል

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ