ዓለም አቀፉ የጀግና ሴቶች ቀን
ዓርብ፣ መጋቢት 22 2009ማስታወቂያ
ዓለም አቀፉ የጀግና ሴቶች ቀን ከ60 በላይ ሃገራት የመጡ ሴቶች በተገኙበት ረቡዕ መጋቢት 20 ቀን በዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ሚኒሥቴር መሥሪያ ቤት ተከብሯል። ከ 100 በላይ ሴቶች የተካፈሉበትን ይህን ዝግጅት በንግግር የከፈቱት አዲስዋ ቀዳማዊት እመቤት ሜሊንያ ትራምፕ ናቸዉ። ሜላንያ ትራምፕ አምባገነን ስርዓትን፤ ጦርነትን ሙስናንና በሴቶች ላይ የሚፈፀመዉን አድሎ ተጋፍጠዋል የተባሉ 13 ሴቶችንም ተሸልመዋል። አንድ የሴቶች ጉዳይ ተሟጋች ጉዳዩን አስመልክተዉ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ማብራርያ በአሉና ሽልማቱ አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል።
መክብብ ሸዋ
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ