1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ቀን

ሐሙስ፣ ኅዳር 30 2008

በመላዉ ዓለም ዛሬ የሰብዓዊ መብት ቀን ታስቦ ዉሎአል። የሰብዓዊ መብት ተማጋቾች ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና አዉሮጳ፤ ስደተኞችን ለመርዳት ያደረገው እንቅስቃሴ እጅግ ጥቄት ነዉ ሲሉ ትችታቸዉን ያሰማሉ። ይህ ትችት ጀርመንንም ቢሆን በጥቄቱ ሳይነካ አላለለፈም።

https://p.dw.com/p/1HLRS
Symbolbild - Flüchtlingslager für Syrer in Jordanien
ምስል picture-alliance/dpa/R. Jensen

[No title]


በጀርመን የዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ዋና ፀሐፊ፤ ለሴልማን ካሊስካን «የስደተኞች ቀዉስ» የሚለዉን ቃል ከአፋቸዉ ማዉጣት ይከብዳቸዋል። በተደጋጋሚ ስለሚወራዉ የስደተኞች ቀዉስ ጉዳይ መስማትም አይፈልጉም። ሴልማን ይህን ቃል እንቀበልም ሲሉ በማስረገጥ ይናገራሉ። እንደ ለሴልማን የሚታየዉ የስደተኞች ቀዉስ ሳይሆን የኃላፊነትን የመወጣትና፤ የርስ በርስ መረዳዳት ያለመቻል ቀዉስ ነዉ። ሴልማን በሰጡት አንድ ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ሕዝብን ለስደት የዳረገዉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መቆም አለበት። ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት «አምነስቲ ኢንተርናሽናል» ጀርመን እያደረገች ስላለዉ ሰብዓዊ እንቅስቃሴ አዎንታዊ ሲል በደረጃ አስቀምጦአታል። ይህ ጉዳይ ሊሳካ የቻለዉ ምንም እንኳ በአስተዳደር ላይ ቀዉስ ቢኖርም በአብዛኛዉ በማኅበረሰቡ ከፍተኛ እገዛ ጥረትና ዝግጁነት ነዉ ሲሉ ሴልሚን ካሊስካን በጀርመን የዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ዋና ፀሐፊ የጀርመንን ሕዝብ ያወድሳሉ።

Selmin Caliskan Amnesty-Mitarbeiterin
ሴልሚን ካሊስካን በጀርመን የዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ዋና ፀሐፊምስል DW/H.Kiesel


« ጀርመን እጅግ ብዙ ጥረትና እንቅስቃሴን እያደረገች ነዉ። በርካታ ሕዝብን ከተቀበሉት በጣም ጥቂት አገራት መካከል አንደኛዋ ጀርመን ነች። በሌላ በኩል ወደ አዉሮጳ ሰዉ እንዳይገባ አዉሮጳ ዙርያ ድንበር እንዲታጠር ጀርመን በመሞከርዋ ቅሪታና ትችት አለን።»


በሌላ በኩል በመንግሥት በኩል እየተደረገ ያለዉ ጥረት የአዉሮጳን የድንበር መዘጋትና ወደ አዉሮጳ በገቡት ስደተኞች ላይ ሁኔታዎችን የማጠጠር ተግባር መታየቱን ሴልማን ይገልፃሉ። በቅርቡ ለስደተኞች በሚሰጠዉ ገንዘብ ሕግን በማክበድ እንዲሁም ስደተኞቹ በሚሸጋገሩትበት ሀገር ማለት «ትራንዚት» ና የመጡበትን ሀገር በተመለከተ የወጣዉን ሕግ የዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ዋና ፀሐፊ ሴልሚን ካሊስካን ትችት ሰንዝረዋል። ዋና ፀሐፊዋ መደረግ ማይገባዉ ነገር ብለዉ ከሚጠቅሱት መካከል ከግብፅ ከኤርትራ እንዲሁም ከሱዳን ጋር የተደረገዉ የጋራ ትብብር ሥራ ተጠቃሽ ነዉ።

Flüchtlinge Boot Meer Griechenland Türkei Ägäis
ስደተኞች በሜዲተራንያን ባህር ላይምስል picture-alliance/dpa/O.Kizil /AA Agency


« እነዚህ አገራት ናቸዉ የሰብዓዊ መብትን በመርገጥ፤ ሕዝብ እንዲሰደድ ምክንያት የሆኑት። ይህ ችግር የሚሸከሙት ደግሞ ስደተኞቹ ናቸዉ። አንዷ ምሳሌ አገር ደግሞ ኤርትራ ናት። ባህርን ተሻግረዉ ወደ አዉሮጳ ከገቡ በርካታ ስደተኞች መካከል በብዛት ሶስተኛዉን ደረጃ የያዙት ኤርትራዉያን ስደተኞች ናቸዉ።»
እንደ ሰብዓዊ ተከራካሪ ድርጅቶች የርስ በርስ ጦርነት በሚታይባቸዉ አገራት በተለይ ደግሞ በሶርያ አስቸኳይ ርዳታ ያስፈልጋል። ከአራት ሚሊዮን በላይ ሶርያዉያን በኢራቅ በዮርዳኖስ፤ ሊባኖስ፤ ግብፅና ቱርክ ከለላ አግኝተዋል። እንድያም ሆኖ በአሁኑ ጊዜ እነዚህ አገራት ስደተኞችን የመቀበል አቅም የላቸዉም። በአሁኑ ሰዓት የሶርያ አዋሳኝ አገራት በሙሉ ከሶርያ የሚያዋስናቸዉን ድንበሮች ሁሉ ዘግተዋል ሲሉ ስለ ስደተኞች ጉዳይ ለዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ተከራካሪ ድርጅት የሚዘግቡት ካሩኒሳ ዳላ ትችት ያሰማሉ።


« የሶርያ አጎራባች አገሮች በሙሉ ማለት ይቻላል በአሁኑ ሰዓት ከሶርያ ጋር ያላቸዉን ድንበሮቻቸዉን ሁሉ ዘግተዋል። በአሁኑ ጊዜ በዮርዳኖስ ድንበር ላይ ወደ 12 ሺህ የሚሆን ሕዝብ ይገኛል። እነዚህ ሰዎች ወዴትም መሄድ አልቻሉም ፤ ሁኔታዉ በጣም ከባድ ነዉ።»
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት በነዚህ አገራት እስከ ሚቀጥለዉ የጎርጎረሳዉያን ዓመት መጨረሻ 10 በመቶ የሚሆኑት ተገን ጠያቄዎች የመኖርያ ቤት እንዲያገኙ ጥሪ አቅርቦአል። ድርጅቱ በተለይ ሴቶች፤ ሕጻናት፤ ህመምተኞችና ግፍ መከራ የደረሰባቸዉ ሰዎች፤ ይህ እድል በቅድምያ እንዲደርሳቸዉ ነዉ ጥሪ ያቀረበዉ። እስካሁን ለ 160 ሺ ስደተኞች ነዉ የመኖርያ ቦታ እንዳለ ይፋ መደረጉ የተነገረዉ። እንድያም ሆኖ በነዚህ መጠለያ ጣብያዎች ርዳታዉ በቂ ባለመሆኑ ሕጻናት ለከባድ ሥራ ተዳርገዋል፤ ይህ ደግሞ ሕጻናት ሴቶች ቶሎ ወደ ትዳር ዓለም እንዲገቡ ይዳርጋል። በመጠለያ ጣብያ ዉስጥ የሚገኙት ሕጻናት መካከል ደግሞ ወደ ትምህርት ቤት የሚሄዱት ገሚሱ ብቻ ናቸዉ። በዚህም ምክንያት ምንም እንኳ ሶርያ ዉስጥ መረጋጋትና ደህንነት ባይኖርም፤ አብዛኞቹ ወደ ሶርያ መመለስስን ይሻሉ። አልያም ህይወታቸዉን ሸጠዉ ወደ አዉሮጳ የሚገቡበትን መንገድ ይፈልጋሉ።

ሃይነ ኪስል / አዜብ ታደሰ

Khairunissa Dahal Amnesty-Mitarbeiterin
ለዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ተከራካሪ ድርጅት ባልደረባምስል DW/H.Kiesel


ሂሩት መለሰ