1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓለም አቀፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ ሰኞ ይጀመራል

ዓርብ፣ ሐምሌ 3 2007

ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ድጋፍ ለዕድገት በሚል ርዕስ በተመድ የተዘጋጀዉ ጉባኤ ሰኞ ሐምሌ ስድስት ቀን 2007 ዓ.ም. አዲስ አበባ ላይ ይጀመራል።

https://p.dw.com/p/1FwcF
Äthiopien Addis Abeba LDG Direktor Tafere Tefachew
ምስል DW/G. Tedla

የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ በላከልን ዘገባ እንደጠቀሰዉ በርካት የሃገራት መሪዎች፣ ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ የተለያዩ ድርጅቶች መሪዎችና ጋዜጠኞች ለስብሰባዉ አዲስ አበባ እየገቡ ነዉ። ከሰኞ ሐምሌ ስድስት አንስቶ ለቀጣይ አራት ቀናት በሚካሄደዉ ጉባኤ ከአምስት ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚገኙም ጌታቸዉ ጨምሮ አመልክቷል። የጉባኤዉን ዝርዝር ዓላማ የሚያመለክት ዘገባ ጌታቸዉ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ