1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓለም ዓቀፉ የወንጀል ችሎትና አፍሪቃዉያን

ዓርብ፣ የካቲት 27 2001

መቀመጫዉ ዘ ሄይግ ኔዘርላንድስ የሆነዉ ዓለም ዓቀፉ ወንጀል ችሎት በሱዳኑ ፕሬዝደንት ላይ የወጣዉን የእስር ማዘዣ የአፍሪቃ መንግስታት ተቃዉመዉታል።

https://p.dw.com/p/H74b
...የተቃዉሞ ሰልፍ በካርቱም...
...የተቃዉሞ ሰልፍ በካርቱም...ምስል AP

በመልካም አስተዳደር፤ በሰብዓዊ መብት ጥበቃ፤ በዴሞክራሲ ግንባታና በልማት ለዉጥ ለመጡ የአፍሪቃ መንግስታት መሪዎች ትልቅ ሽልማት የሚሰጠዉ የሞ ኢብራሂም ድርጅት መስራችና መሪ ሞ ኢብራሂምና በዚሁ ድርጅት የአዉሮጳዉያኑ 2008ዓ,ም ተሸላሚ የሆኑት የቦትስዋና ፕሬዝደንትም ችሎቱ ወጥና ነፃ ፍርድ መስጠቱን በመጠራጠር ዉሳኔዉ ተቀባይነት የለዉም ነዉ ያሉት።