1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓለም ዓቀፍ ቀይመስቀል እና አፍሪቃ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 20 2003

የዓለም ዓቀፍ ቀይመስቀል ማኅበር ፕሬዝደንት ዣኮብ ኬለንበርገር፤

https://p.dw.com/p/RKuh
ምስል picture alliance / dpa

ሰብዓዊ ቀዉስ እንደታየበት በሚነገረዉ የሊቢያ ግጭትና ጦርነት ጉዳይ ለመነጋገር አዲስ አበባ እንደሚገኙ ከአዲስ አበባ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ በላከልን ዘገባ አመልክቷል። ዛሬ ከአፍሪቃ ኅብረት ባለስልጣናት ጋ እንደሚነጋገሩ የሚጠበቀዉ ኬለንበርገር ትናንት ከኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር በተለያዩ የጋራ ጉዳዮች ላይ መምከራቸዉን ዘገባዉ ጨምሮ ገልጿል። የዓለም ዓቀፉ ቀይ መስቀል ፕሬዝደንት በአዲስ አበባ ከሰነበቱት የሊቢያ ተቃዋሚ ኃይሎች ጋ በተለያየ ጊዜ መምከራቸዉን የገለፁ ሲሆን በተለይ በሚስራታ ያለዉ ሰብዓዊ ቀዉስ እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ መጠቆማቸዉን የወኪላችን ዘገባ ያስረዳል።

ዝርዝር ዘገባዉ እነሆ!

ታደሰ እንግዳዉ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ