1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓለም ዓቀፍ ትብብር ለትምህርት

ሰኞ፣ ሰኔ 23 2006

60 ለሚደርሱ አዳጊ ሃገራት የትምህርት መርሃ ግብር መርጃ የሚውል የ28.5 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ለመስጠት ቃል መገባቱ ተገለፀ ።

https://p.dw.com/p/1CSpF
ምስል picture-alliance / Godong

«ዓለም ዓቀፍ ትብብር ለትምህርት» የተባለው ድሃ ሃገራት ትምህርትን በነፃ ለማዳረስ እንዲችሉ ለማገዝ የተቋቋመው ድርጅት ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ጋር በጋራ ብራሰል ቤልጂግ ውስጥ በጠራው የለጋሾች ጉባኤ ላይ እንደተገለፀው እርዳታውን ለመስጠታ ቃል የተገባው በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ነው ።የበርካታ ሃገራት የትምህርትና የልማት ሚኒስትሮች የእርዳታ ድርጅቶችና የመንግሥታቱ ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ800 የሚበልጡ የትምህርት ባለሞያዎችና ባለሥልጣኖች በተሳተፉበት በዚሁ ጉባኤ ላይ ታዳጊ ሃገራትም ለትምህርት የሚመድቡትን ገንዘብ መጠን ከፍ ለማድረግ መስማማታቸው ተመልክቷል ።

ገበያው ንጉሴ

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ