1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓመታዊዉ የሐጂ ስርዓትና ኢትዮጵያዉያን

ሰኞ፣ መስከረም 2 2009

በሳዑዲ ዓረቢያ መካ 8 ሺህ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ከ 2 ሚሊዮን በላይ ሙስሊሞች ዓመታዊውን የሐጂ ስርዓት እያከናወኑ ናቸው፡፡ በመስተንግዶ እና ደህንነትን በማስጠበቅ በኩል በተለይ በኢራን ባለስልጣናት ዘንድ ዘወትር የምትወቀሰው ሳዑዲ አረቢያ ለዘንድሮው ሐጅ የምመናኑን ማንነትና የጤና ሆኔታ የሚያሳይ ዘመናዊ ጂፒኤስ የተገጠመለት አምባር

https://p.dw.com/p/1K0ll
Saudi-Arabien Hadsch - PilgerInnen in Mekka
ምስል Reuters/A. Jadallah

[No title]

በየምዕመኑ እጅ ላይ እንዲታሰር አድርጋለች፡፡ ይሁን እንጂ የኢራኑ አያቶላ እና የሳዑዲ ዓረቢያው ታላቁ ሙፍቲህ ዘንድሮም የመረሩ ቃላትን ተወራውረዋል ፡፡ የዘንድሮው ሐጅ ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ድረስ የከፋ አደጋ አልተሰማበትም፡፡ ነገር ግን እስከ አሁን ድረስ 133 ምዕመናን ሕይወታቸው አልፏል 213ቱ ደግሞ ለሆስፒታል አልጋ ተዳርገዋል ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከእድሜ መግፋት ጋር የተያያዙ የልብ እና የሳንባ ህመም ናቸው፡፡ በሪያድ የሚኖሩ ከአንድ መቶ በላይ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ማለዳ ከኢድ ጸሎት በኋላ በጋራ በመሆን የኢትዮጵያ መንግስት በዜጎች ላይ የሚፈጽመውን ግድያ እንዲያቆም ጠየቀዋል፡፡

ስለሺ ሽብሩ
አዜብ ታደሰ