1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዕቅዱ ጥሩ ቢሆንም ሙሉ ስኬት ግን አልታየበትም

ዓርብ፣ መስከረም 21 2008

በያዝነዉ የጎርጎረሳዊ 2015 ዓ,ም መጨረሻ የተመድ የምዕተ ዓመቱ የልማት እቅድ ማስፈፀምያ ቀነ ቀጠሮ ይጠቃለላል። ዕቅዱ በ 2015 መጨረሻ በዓለማችን ላይ የሚታየዉን ድህነት ግማሽ በግማሽ በመቀነስ ረኃብን በገሚስ መቅረፍ ማስቻል ነዉ። በዚህ ዕቅድ አንዳንድ በሽታዎች የመዛመት ፍጥነታቸዉን ለመግታት አስችሎአል።

https://p.dw.com/p/1GhYa
Irakkrieg Armut Kinder
ምስል picture-alliance/dpa/S. Reboredo

[No title]

ለምኃሌ በዚህ ዕቅድ እንደ HIV/ኤድስ እና የወባ በሽታን የመሳሰሉት በመጠኑም ቢሆን የመዛመት ፍጥነታቸዉን ለመግታት አስችሎአል። ቢሆንም ግን የምዕተ ዓመቱ እቅድ ዉጤት በአጠቃላይ ሲገመገም የተደባለቀ ዓይነት ዉጤት ነዉ የሚታይበት ስትል የዶይቼ ቬለዋ ሄለ ጃፕሴን ዘግባለች።

«ማቅረብ የምንችለዉ የተመድ ከፍተኛ ስኬት» ይላል በበርሊን የሥነ- ሕዝብ እና ልማት ተቋም ተጠሪ ራይነር ክሊንግ ሆልዝ ስለተመድ የምዕተ ዓመቱ ግብ የቀረበ የጥናት ግምገማ ርዕስ። ከጎርጎረሳዊዉ 2000 ዓ,ም ጀምሮ የመንግሥታቱ ድርጅት ካቀዳቸዉ ስምንት የልማት ግቦች በመላዉ ዓለም ለሚደረገዉ የልማት ትብብር ሥራ አመላካች መንገድ ነበሩ። የመንግሥታቱ ድርጅት በመጨረሻዉ የማጠቃለያ መግለጫዉ ከፍተኛ ዉጤት እንደተገኘ ነዉ ይፋ ያደረገዉ።

Indien Zwei Marktfrauen in Meghalaya
ምስል DW/H. Jeppesen

«የምዕተ ዓመቱ የልማት እቅድ እጅግ ጠንካራ ነበር። ምክንያቱም ዕቅዱ በመላዉ ዓለም ድህነትን ለመዋጋት ያለመ በመሆኑ ነዉ። በፖለቲካና በፋይናንስ ረገድ ሊተገበር በሚቻል ዕቅዶች ላይ ድህነትን ለመቅረፍ በተለያዬ ዘዴዎች የታለመበት ነዉ። »

ሲሉ ነበር በተመ የልማት መረሃ-ግብር የ2015 ቱ ቡድን መሪ ፓዉል ላድ የተናገሩት። የተመድ ከጎርጎረሱ 1990 ዓ,ም አንስቶ ዓለም ከፍተኛ ድህነትን መቀነስ ይችላል ሲል በእቅድ አስቀምጦአል። በቀን ከ 1, 25 ዶላር ያነሰ ገቢ ያለዉ እጅግ ድሃ በሚለዉ መዘርዝር መረጃም ተቀምጦአል። ይህ የሚታየዉን ከፍተኛ ድህነት በከፊል መቀነስ የሚለዉን የምዕተ ዓመቱ ግብ ከሦስት ዓመት በፊት ዉጤት አሳይቷል። Global Policy Forum የተባለዉ በቦን ጀርመን የሚገኘዉ የተመድ ሥራዎችን የሚቆጣጠረዉ ገለልተኛ ተቋም ተጠሪ ዬንስ ማርቲን እንዳሉት በዓለማችን ድህነትን ለመቅረፍ የተደረገዉ ርምጃ አመርቂ ቢሆንም ድህነትን ለማጥፋት በቀጣይ መሠራት ይኖርበታል።

« ስኬቱ በከፊልም ቢሆን ተጋኖ እና ተሸላልሞ መቅረቡን እናያለን። በቀን 1,26 ዶላር ገቢ ያላቸዉ ሰዎች አሁንም ቢሆን ጥሩ በሆነ የሰዉ ልጅ ሰብዕና በተጠበቀበት መልኩ እንደማይኖሩ እናዉቃለን።»

ዬንስ ማርቲን በመቀጠል፤ እንደተናገሩት ግቡን ቀንሶ ማስቀመጥ ድህነት ተቀረፈ ማለት አይደለም።

« ድህነትን ለመቀነስ ግቡን ቀንሶ ማስቀመጡ በዓለም ላይ የሰዎች ኑሮ ተሻሻለ ማለት አይደለም።»

በዓለማችን ረሃብን በግማሽ መቀነስ የሚለዉ የተመድ የምዕተ ዓመቱ ግብ፤ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ አልሆነም። በጎርጎሪዮሳዊዉ 1990 ዓ,ም ከአራት ሰዉ አንዱ ረሃብተኛ ነበር። ዛሬ ከስምንቱ ሰዉ አንዱ ረሃብተኛ ነዉ። የጀርመኑ ግብረ-ሰናይ ድርጅት የቬልት ሁንገር ሂልፈ ፕሬዚዳንት ቤርብል ዲክማን በመላዉ ዓለም አሁንም ወደ 800 ሚሊዮን ሕዝብ ረሃብተኛ ነዉ ሲሉ ይወቅሳሉ።

Zum Thema Afghanistan - Die deutschen Entwicklungshelfer bleiben
ምስል picture-alliance/dpa

«795 ሚሊዮን ሕዝብ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ነዉ። እኛን ይበልጥ ጥያቄ የሚያጭርብን፤ አሁን በዚህ ፍጥነትና በአዲስ የልማት ግብ እስከ 2030 ዓ,ም ድህነትን ለመቅረፍ ግብ መያዛችን ነዉ። ይህን ግብ የምንደርስበት አይሆንም። »

የተመድ አሁን ባለዉ ዘላቂ የልማት ግብ እስከ 2030 ረሃብና የምግብ እጥረትን ከምድረ-ገጽ ለማጥፋት እቅድ ይዟል። ግቡ ይሳካል በተባለበት ዓመት በመላዉ ዓለም በቂ ምግብ ይኖራል ነዉ ተስፋዉ። ግን እስካሁን ይህ ያልተሳካበት ምክንያት ችግሮች በመኖራቸዉ ነዉ። እንደ ዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት «FAO» ጥናት መዘርዝር መሠረትም በአንድ በኩል በምግብ ስርጭትና ምግብ ማከማቸት ረገድ ችግሩ ባለመወገዱ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በመላዉ ዓለም ከሚመረተዉ ምግብ አንድ ሦስተኛዉ ተበላሽቶ በመዉደቁ ነዉ።

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ