1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዚምባብዌና የብሄራዊ አንድነቱ መንግስት

ቅዳሜ፣ የካቲት 7 2001

አዲሱ የዚምባብዌ ጠቅላይ ሚንስትር ባለፈው ረቡዕ ቃለ መሀላ በፈጸሙበት ጊዜ ዚምባብዌን ቀድሞ ወደነበረችበት ደረጃ መመለስ የሁሉም ግዴታ መሆኑን አሳስበዋል።

https://p.dw.com/p/GtrT
ሞርገን ቻንጊራይ
ሞርገን ቻንጊራይምስል AP

የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ሮበርት ሙጋቤም ለብዙ ጊዜ ተቀናቃኛቸው ሆነው ከቆዩት ከጠቅላይ ሚንስትር ሞርገን ቻንጊራይ ጋር ተባብረው በመስራት ሀገራቸውን ከገጠማት ችግር ለማላቀቅ ዝግጁ መሆናቸውን በዚሁ ጊዜ አረጋግጠውላቸዋል። ለዚሁ ዓላማ መሳካትም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ርዳታ አስፈላጊ እንደሚሆን ቻንጊራይ በማስታወቅ የርዳታ ጥሪያቸውን አስተጋብተዋል።

RTR,DPA, DW

AA, SL