1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዚምባብዌና የአውሮጳ ህብረት ውሳኔ

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 21 2004

የአውሮጳ ህብረት በዚምባብዌ ላይ የጣለውን ጠንካራ ማዕቀብ በከፊል አነሳ። ህብረቱ ከአንድ አሠርተ ዓመት በፊት በዚችው ሀገር ላይ የወሰደውን የማዕቀብ ርምጃ አሁን በከፊል ለማንሳት የወሰነው ሀገሪቱ የጀመረችውን የማዕቀብ ዴሞክራሲያዊ ሂደት ለማበረታታት በማሰብ ነው።

https://p.dw.com/p/15g1b
ፕሪዚደንት ሮበርት ሙጋቤና፤የዚምባብዌ ጠ/ሚ ሞርገን ቻንገራይምስል AP

የአውሮጳ ህብረት በዚምባብዌ ላይ የጣለውን ጠንካራ ማዕቀብ በከፊል አነሳ። ህብረቱ ከአንድ አሠርተ ዓመት በፊት በዚችው ሀገር ላይ የወሰደውን የማዕቀብ ርምጃ አሁን በከፊል ለማንሳት የወሰነው ሀገሪቱ የጀመረችውን የማዕቀብ ዴሞክራሲያዊ ሂደት ለማበረታታት በማሰብ ነው።

ዚምባብዌ በቅርቡ በሃገርዋ በአዲስ ህገ መንግስት ረቂቅ ላይ ህዝበ ዉሳኔ ለማካሄድ የወጠነችዉ እቅድዋ ከህብረቱ በኩል ሞገስ አግኝቶአል። ይሁን እና አዲስ የተረቀቀዉ ህገ መንግስት ፕሪዚደንት ሮበርት ሙጋቤን ወደፊትም በስልጣን ለማቆየት የታሰበ ነዉ በሚል፤ ሃያስያን ወቀሳ አሰምተዋል። ህብረቱ በደረሰዉ ዉሳኔ መሰረት፤ ዚምባብዌ የልማቱን እርዳታ ከህብረቱ እንደገና ታገኛለች። በሙጋቤ እና በ 100 የቅርብ ረዳቶቻቸዉ ላይ የተጣለዉ የጉዞ እገዳ ግን እንደጸና ይቆያል። በዚምባብዌ መዲና ሃራሪ የአዉሮጳ ህብረት አምባሳደር አልዶ ዴል አሪቺዮ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ማዕቀቡ በጠቅላላ ሊነሳ የሚችልበት ሁኔታ መኖሩን አስታዉቀዋል።

Zimbabwe Afrika Armut
ምስል AP

«በሰላማዊ እና በሚታመን ህገ መንግስት ረቂቅ ላይ ካለ ሃይሉ ተግባር እና ካለማስፈራራት እርምጃ ዉሳኔ ህዝብ የሚካሄድ ከሆነ፤ በተናጠል በግለሰቦች ላይ የተጣለዉ ማዕቀብንም፤ ለማንሳት ስምምነት ተደርሶአል።» የፕሪዚደንት ሙጋቤ ፓርቲ የህብረቱን ዉሳኔ በተመለከተ፤ የተጠበቀዉን አስተያየት ሰጥቶአል። ከፊሉን ማዕቀብ ለማንሳት ህብረቱ የደረሰዉ ዉሳኔ፤ ግንኙነቱ ለሚሻሻልበት ድርጊት፤ ወሳኝ ምልክት ያስተላለፈ ቢሆንም፤ ዉሳኔዉ እንደሚፈለገዉ ርቆ የሄደ አይደለም፤ በሚል የዚምባብዌ የፍትህ ም/ር ቺና ማሳ ፓትሪክ ወቀሳ አሰምተዋል።

« ማዕቀቡ በጠቅላላ ያላንዳች ቅድመ ግዴታ እንዲነሳ ነዉ የምንጠይቀዉ ምክንያቱም ህገ ወጥ ነዉና» የአፍሪቃ ህብረት፤ ደቡብ አፍሪቃ፣ ቦትስዋና እንዲሁም የፕሪዚደንት ሮበርት ሙጋቤ ዋንኛ ተፎካካሪ፣ የዚምባብዌ ጠ/ሚ ሞርገን ቻንገራይ ሳይቀሩ በዚምባብዌ ላይ የተጣለዉ ማዕቀብ በጠቅላላ እንዲነሳ አጥብቀዉ እየጠየቁ ነዉ። ጠ/ሚ ሞርገን ቻንገራይ እንዳመለከቱትም፤ ማዕቀቡ ግዜ ያለፈበት ነዉ። « ወንድም ወንድሙን የገደለበት አስከፊ የታሪክ ምዕራፍ ማሳላፋችንን፤ በሚገባ አዉቃለሁ። አሁን ግን ፤አፍሪቃ የረሃብ የድህነት እና የበሽታዎች አህጉር ሳትሆን አዳዲስ እድል የሚፈጠርባት አህጉር ናት ብለዉ ብዙዎች ማመን በጀመሩበት ግዜ ዉስጥ ነዉ የምንገኘዉ፤ እና ዚምባብዌ ተገላ ከዉጭ ተመልካች በመሆን ፈንታ ከመሪዎቹ አንቀሳቃሾች መካከል፤ ለመቆጠር ነዉ የምትፈልገዉ። ከጥቂት ግዜ በፊት ወደ ዚምባብዌ በመሄድ ሁኔታዎችን የተመለከቱት፤ የተመድ የሰብአዊ መብት ም/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ናቪ ፒላይ በአዲሱ ህገ መንግስት ረቂቅ ላይ፤ ዉሳኔ ህዝቡ እንደተጠበቀዉ በሰላማዊ እና በትክክለኛ ዘዴ ከተካሄደ የአዉሮጳ ህብረት የማዕቀብ ዉሳኔዉን፤ እንደገና እንዲያጤነዉ ጠይቀዋል።

An unidentified man reads the Zimbabwean State owned daily newspaper, The Herald, in Harare, Zimbabwe Saturday, May, 3, 2008. On Friday, the Zimbabwe Electoral Commission released results from the March 29 presidential election that showed opposition leader Morgan Tsvangirai winning the most votes, but not the simple majority needed to avoid a runoff with President Robert Mugabe, the second-place finisher. The opposition rejected the results as fraudulent. (AP Photo/Tsvangirayi Mukwazhi)
ምስል AP

የአዉሮጳ ህብረት ከፊሉን ማዕቀብ ለማንንሳት የወሰነበት እርምጃ፤ የተቻኮለ እንዳልሆነ፤ ዚምባብዌ ዜጎች ተስፋ አድርገዋል። የዚምባብዌ መንግስት ባወጣዉ እቅድ መሰረት በአዲሱ ህገ መንግስት ረቂቅ ላይ ዉሳኔ ህዝቡ የፊታችን ጥቅምት ወር ከተካሄደ ከስድስት ወራት በኋላ በሃገሪቱ ለመጀመርያ ግዜ ነፃ እና ትክክለኛ ምርጫ ለማካሄድ ወስኖአል።

ክላውስ ሽቴከር/አርያም ተክሌ

መሥፍን መኮንን