1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዛምቢያ እና ከጸሀይ የሚገኝ የኃይል ምንጭ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 17 2000

ባለፈው ጥቅምት ወር የኖቤል ሰላም ተሸላሚ የሆኑት አሜሪካዊው አል ጎር ወጣቶች ከከሰል የሚወጣ የኃይል ማመንጫ ተቋም ግንባታን ወይም ቡልዶዘሮችን የማያስቆሙበት ድርጊት እንዳልገባቸው ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/E0mm
ሶላር ሴል
ሶላር ሴልምስል Q-Cells

የአሁኑ ጊዜ ወጣቶች በተፈጥሮ አካባቢ ብክለት አንጻር ተቃውሞ ለማሰማትም አደባባይ አይወጡም፤ ይሁንና፡ በትንንሾቹ ፕሮዤዎች አማካይነት ርምጃ ይወስዳሉ። ለዚህም በጀርመን የሩር አካባቢ የሚኖሩ ወጣቶች እንደምሳሌ ይጠቀሳሉ። ወጣቶቹ ከጸሀይ ጨረር የሚገኝ የኃይል ምንጭ ተቋም ገንብተዋል። ይህንኑ ታታሪነታቸውንና ችሎታቸውንም ወደ አፍሪቃ ይልካሉ። በዚህ ሳምንት በተከታታይ ከሚቀርበው ከተፈጥሮ አካባቢ ጋር ከተያያዘው ዝግጅታችን ለዛሬ የምናስደምጣችሁ የሩር አካባቢ ጀርመናውያን ወጣቶች ስለጀመሩት ፕሮዤ ይሆናል። አርያም ተክሌ

አንድ ቀን ሀሙስ፡ ከጥዋቱ አራት ሰዓት ላይ በግላድቤክ ከተማ የሚገኘው የኢንገቦርክ ድሬቪትስ አጠቃላይ ትምህርት ቤት አስራ ሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች የቴክኒክ መምህሩ ፔተር ማርቲን ለተማሮቻቸው ትንሾቹን ጥቁር ግራጫ መጻፊያ ቦታ የያዙ የእንጨት ሰሌዳዎችን፡ እንዲሁም ቀይና ሰማያዊ ሽቦዎችንና አንድ መለኪያ መሳሪያ አድለው፣ ተማሮቹን

« እያንዳንዳችሁ ሁለት በጸሀይ ጨረር የሚሰሩ ሴሎችን አውጡና ለኩ »
ሲሉ ያሳስባሉ።
ተማሪው ዬንስ ክራውዘም፡
« ይህ ነው የኤሌክትሪክ ኃይልና ጥንካሬ የሚለካበት ሜትር ካለ በኋላ አንዱ በጸሀይ ኃይል የሚሰራው ሴል ቮልት ጥንካሬ እንዳለው አስታወቀ። »
የንስ ክራውዘና አቻዎቹ ሴሎቹን ከለኩ በኋላ የአንዱ በጸሀይ ኃይል የሚሰራው ሴል ቮልት ያን ያህል ጠንካራ እንዳልሆነ፡ ግን ስድስቱ በጸሀይ ኃይል የሚሰሩ ሴሎች አንድ ኤም ፒ 3 የሙዚቃ መሳሪያ ማጫወት እንደሚችል ተገንዝበዋል። ለመጀመሪያ ጊዜም፡ ክራውዘ እንደገለጸው፡ ተማሪዎቹ ይህ እንዴት እንደሚሰራ ለመረዳት ችለዋል። በአንድeበጸሀይ ኃይል በሚሰራ ሴል ብቻ ሁነኛ ውጤት ማስገኘት ስለማይቻል ተማሪዎቹ አንድ ትልቅ አውታር ለመገንባት በመወሰን፡ አርባ ካሬሜትር ስፋት ባለው የትምህርት ቤታቸው ጣራ ላይ አንድ በጸሀይ ኃይል የሚሰራ የኃይል ማምረቻ አውታር ተክልዋል።
« አትሞ »
ዕቅዱን ያወጡትና ግንባታውን በጠቅላላ የሰሩት የቴክኒክ ትምህርት የሚከታተሉት ተማሮቹ ናቸው። በዚህም ኣካይነት፡ ትምህርት ቤቱ አሁን ከሚያስፈልገው የኃይል ምንጭ መካከል ከፊሉን ራሱ ማምረት የጀመረ ሲሆን፡ አውታሩ ከተተከለ አንስቶ ወደ ክበበ አየሩ ከሚተነው የተቃጠለ አየር መካከል 1400 ኪሎ ለመቀነስ ችሎዋል። »
የፕሮዤው ዓላማ ግን ይህ ብቻ አለመሆኑን መምህሩ ፔተር ማርቲን ገልጸዋል።

« የዚህ ዓይነቱ ትምህርት የሚጠቅመው የአየር ብክለት ስለሚያስከትለው ችግር በጊዜ ለማሳወቅና ቴክኒክ በዚህ አንጻር ምን ማድረግ እንደሚችል ለማሳየት ነው። ይህ ወጣቶቹ ወደስራው ዓለም በሚሄዱበት ጊዜ፡ በዚሁ ዘርፍ እንዲሰማሩ ትልቅ ዕድል ይከፍትላቸዋል፤ ይህ ዓይነቱ ስራ በመላው ዓለም አስፈላጊ ነውና። »

የአየር ፀባይ ለውጥ ጉዳይ በወጣቶቹ ዘንድ ትልቅ ቦታ ይዞዋል። ዩሊያ ፎን ግራዶቭስኪም ስለሁኔታው ማሰላሰልዋ እንዳልቀረ ገልጻለች።
« የማዮርካን ማዕበል በቴሌቪዥን በምመለከትበት ጊዜ፡ ይህ ዓይነቱን ሁኔታ ለመቀየር ሁላችንም ተባብረን አንድ ለውጥ ማድረግ እንዳለብን ይሰማኛል፤ ግን ምንም ሲደረግ ስላላየሁ፡ ወደፊት ለውጥ ሊደረግ አይችል ይሆናል በሚል መስጋቴ አልቀረም። »

በዚህም የተነሳ የግላድቤክ አጠቃላይ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በትምህርት ቤታቸው ጣራ ላይ የተከሉትን ዓይነት በበጸሀይ ኃይል የሚሰራ አውታር አፍሪቃ ውስጥ ተጓዳኝ በሆነው አንድ የዛምቢያ ትምህርት ቤትም ተክለዋል። ባለፈው የክረምት ወራት ነበር ስድስት የግላድቤክ ተማሪዎችና የቴክኒክ መምህር ጉንትራም ዛይፐል ወደ ማቻ፡ ዛምቢያ በመሄድ አውታሩን የተከሉት።vከጸሀይ የሚገኝ የኃይል ምንጭ አስተማማኙ የኮሬንቲ መረብ ለሌለባትና ከፍተኛ የጸሀይ ጨረር ላለባት ዛምቢያ የሚያስገኘው ጥቅም ከፍ ያለ መሆኑን ዛይፐል አስረድተዋል። ወደዛምቢያ የሄዱት ተማሮች እንደታዘቡት፡ ሰማንያ ከመቶ የሚሆነው ህዝብዋ በየቀኑ ከአንድ ዶላር ባነሰ ገቢ በሚኖርባት ዛምቢያ ውስጥ የተፈጥሮ አካባቢ እንክብካቤና የአየር ጸባይ ለውጥ ቀዳሚ ትኩረት አላገኘም። ሶስት የኃይል ማመንጫ ተቋም ብቻ ያላት የዛምቢያ ህዝብ ለምግብ ማብሰያ ከሚጠቀምበት የማገዶ እንጨት የሚታነው ጭስ የተፈጥሮ አካባቢውን እየበከለ ተገኝቶዋል። በዚህም የተነሳ ሌላ አማራጭ የኃይል ምንጭ መፈለጉ አስፈላጊ መሆኑን ተማሮቹ አምነውበታል።
ጀርመናውያኑ ተማሪዎች በዛምቢያ የተከሉት በጸሀይ የሚሰራው የኃይል ማመንጫ አውታር የዛምቢያው ትምህርት ቤት ለኮሬንቲ አቅርቦቱ አስተማማኝ ባልሆነው የሀገሪቱ መረብ ላይ የነበረውን ጥገኝነት አላቆት ራሱን እንዲችል አድርጎታል። ከዚህ በተረፈም ጀርመናውያኑና ዛምቢያውያኑ ተማሪዎች የአየር ጸባይን በትንሾቹ ፕሮዤዎች አማካይነትም መንከባከብ እንደሚቻል ለመማር መቻላቸውን መምህሩ ፔተር ማርቲን አስረድተዋል። ሊረሳ የማይገባው፡ ይላሉ ፔተር ማርቲን፡ እነዚህ ተማሪዎች በአየር ጸባይ እንክብካቤ ረገድ ወላጆቻቸው ለፈጸሙት ጥፋት መዘዙን መቀበል ያለበት ትውልድ ከፊል ናቸውና።