1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዜድቲኢ ኩባንያ እና ከስራ የተሰናበቱት ሰራተኞቹ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 9 2004

ዜድቲኢ ( ኤችኬ ) ሊሚትድ ኢትዮጵያ ከተባለዉ የቻይና ኩባንያ በተለይ በፅዳት እና በምግብ አብሳይነት የተሰማሩ 59 የሚሆኑ ሠራተኞች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ከስራ ገበታቸው ተሰናብተዋል።

https://p.dw.com/p/15q0h
China-Afrika-Forum in Peking Local residents pass billboards promoting the China Africa Summit Tuesday 31 October 2006. The summit begins tomorrow 01 November and goes on until 06 November bringing together leaders and high officials from most African countries to gather in Beijing in the spirit of new cooperation between the Asian economic power and the entire African continent. EPA/ADRIAN BRADSHAW +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture-alliance/ dpa

ዜድቲኢ ( ኤችኬ ) ሊሚትድ ኢትዮጵያ- ኢትዮጵያ ዉስጥ በቴሌኮም ሥራ ላይ የተሰማራ የቻይና ኩባንያ ነው። የሠራተኛ ማህበር ሊቀመንበር ፤ አቶ እምባይብል አበበ እንደሚሉት ኩባንያዉ የስንበት ደብዳቤ ባገኙ ማግስት 59 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊ ሠራተኞቹን ከሥራ አሰናብቷል። የመስሪያ ቤቱ የአገር ውስጥ ጉዳዮች የሠራተኛ አስተዳደር ኃላፊ አቶ ሔኖክ ወንድማገኝ ፤ ሠራተኞቹ ከሥራ የተሰናበቱበትን ዋና ምክንያት እንዲገልፁልን ጠይቀናቸዋል።

A Chinese construction worker supervise the building of a road, Thursday, April 26, 2007 in the Ethiopian capital, Addis Ababa. China said Thursday that a deadly attack in Ethiopia that killed 74 people, including nine Chinese, will not stop it from investing in Africa, but added it planned to boost security measures. (ddp images/AP Photo/Karel Prinsloo)
ቻይናውያን በአፍሪቃምስል AP

ሠራተኞቹ በሥራ ገበታ ሳሉም ብዙ ያልተሟላቸው ነገር እንደነበር፤ አንዲት ወይዘሮ ነግረውናል። ምንም አይነት የሠራተኛ መታወቂያም ሆነ የውልና የቅጥር ደብዳቤ አልነበረንም ነው ያሉት። አሁን ደግሞ ባንዴ ከሥራ መሰናበታቸውን ለዶይቸ ቬለ አስረድተዋል። ኩባንያው በበኩሉ፤ ለሠራተኞች የሚገባውን በሙሉ እንዳደረገ እና በገጠመው የሥራ ሂደት ማሻሻል ሠራተኞቹን እንዳሰናበተ ይናገራል። ከሥራ የተሰናበቱ ሠራተኞችም የሰጡን አስተያየት አለ።

እስከ ቅርብ ቀናት የሠራተኛ ማህበር ሊቀመንበር ኃላፊ የነበሩት ፤ አቶ እምባይብልም ኩባንያው ህግ እንደማያከብር፤ ምንም አይነት የእውቀት ልውውጥ እንደማይደረግ እና ኢትዮጵያዊው ተቀጣሪ ቁጥር በአንፃሩ ትንሽ ነው ይላሉ።

South African President Jacob Zuma, left, is greeted by Chinese President Hu Jintao, center, while Benin's President Thomas Yayi Boni, right, looks on after Zuma delivered a speech for the 5th Ministerial Conference of the Forum on China-Africa Cooperation held at the Great Hall of the People in Beijing, China Thursday, July 19, 2012. Hu on Thursday pledged African governments $20 billion in credit over the next three years and called for more China-Africa coordination in international affairs to defend against the "bullying" of richer powers. (Foto:Andy Wong/AP/dapd)
የቻይና መንግስት ከአፍሪቃ መንግስታት ጋ ያለውን ስራ ሁሌ እያጠናከረ ነው።ምስል dapd

ተቀጣሪዎቹ የጤና መድህን ዋስትና ስለሌላቸው ከኩባንያው ጋ ስምምነት ባለው ሀያት ሆስቲታል ሳይሆን በግላቸው ሌላ ቦታ ታክመው ሂሳቡ እንደሚወራረድላቸው ሲገልፁ አቶ ሔኖክ ይህንን በማጣጣል ሠራተኞቹ በሀያት ሆስቲታልም በግልም መታከም እንደሚችሉ እና ሂሳቡ እንደሚከፈል ነው ያሳወቁን። ኩባንያው ህግ አያከብርም ለሚለው ወቀሳ አቶ ሔኖክ መልሳቸው ምንድን ነው? ይህ ኩባንያስ በኢትዮጵያ ህግ እና ደንብ መሠረት መሥራት አልነበረበትም ወይ?

ለጥያቄዎቻችን በሙሉ ያገኘነቸውን መልሶች ከሙሉ ዘገባው ያድምጡ ።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሠ