1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዞን ዘጠኞች ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 21 2009

ፍርድ ቤቱ የስር ፍርድ ቤት ለሰጠው ፍርድ መሠረት የሆኑ የሲዲ እና የሰነድ ማስረጃዎች አላገኘንም በሚል ብይኑን አስተላልፏል ።

https://p.dw.com/p/2V3aF
Symbolbild Gericht Gesetz Waage und Hammer
ምስል Fotolia/Sebastian Duda

Beri AA(Zone 9 court hearing) - MP3-Stereo

ዛሬ ያስቻለው የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዞን ዘጠኝ በመባል የሚጠራው የድረ ገፅ ፀሀፍት ቡድን አባላት ላይ አቃቤ ህግ ላቀረበው ይግባኝ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ ። ፍርድ ቤቱ  ዛሬ ብይን ይሰጣል ተብሎ ተጠብቆ ነበር ። ይሁን እና የስር ፍርድ ቤት ለሰጠው ፍርድ መሠረት የሆኑ የሲዲ እና የሰነድ ማስረጃዎች አላገኘንም በሚል ብይኑን አስተላልፏል ። ከዞን ዘጠኝ አባላት አንዱ ለዶቼቬለ እንደተናገረው ፍርድ ቤቱ ቤቱ አልደረሰኝም ካላቸው መረጃዎች አንዱ ሀገር ውስጥ የሚገኙትን የዞን ዘጠኝ አባላት አይመለከትም ። ዝርዝሩን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ልኮልናል ። 
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ