1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሀይንሪሽ በል ድርጅት በኢትዮጵያ

ሐሙስ፣ ጥር 13 2002

ከጀርመን የፖለቲካ ፓርቲዎች ለአካባቢ ጥበቃ ልዩ ትኩረት በመስጠት ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዘው የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ Heinrich Böll በተባለው ድርጅቱ አማካይነት በተለያዩ አገራት በዋነኛነት ለዲሞክራሲ መስፋፋት ለሴቶች ዕኩልነት መከበርና እና ለአካባቢ ጥበቃ ልዩ ልዩ ድጋፎችን በመስጠት ላይ ይገኛል ።

https://p.dw.com/p/LdDk
Heinrich Böllምስል dpa

የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ ሀሳብ አመንጪ በሆኑት በታዋቂው ጀርመናዊ ደራሲ Heinrich Böll የተሰየመው ይኽው ድርጅት ከሚንቀሳቀስባቸው አገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት ። በዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን የሀይንሪሽ በል ድርጅት በኢትዮጵያ ስለሚያከናውናቸው ተግባራት ሳምንት በይደር ያቆየነው ቀሪ መሳናዶ አለን ።

Türkische Immigranten in Deutschland, München
የቱርክ ዜጎች በጀርመንምስል AP

ጀርመን ውስጥ ከአጠቃላዩ ሰራተኛ በመቶ ሲሰላ እጅግ ጥቂት የሆነውን በአገልግሎት መስጫ ዘርፍ የተሰማራውን የውጭ ዜጋ ቁጥር ከፍ ለማድረግ የቀረበ አንድ አዲስ ሀሳብ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ ። በጀርመን የውጭ ዜጎች ከህብረተሰቡ ጋር ተቀራርበው የሚኖሩበትን መንገድ በሚያመቻቸው ኮሚሽን ኮሚሽነር ማርያ ቦህመር Maria Boehmer የቀረበው ይኽው ሀሳብ የጀርመን ፖለቲከኞችን ድጋፍ አላገኘም ።

ሂሩት መለሰ