1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሀገር ዉስጥ ወቅታዊ ጉዳዮች

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 26 2005

በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድ ሙስሊም ምዕመናን የሚያሰሙት የተቃዉሞ ድምፅ ቀጥሏል። በተመሳሳይ ሁኔታ ሀረር ዉስጥ መስጊድ በፖሊስና በሙስሊም ምዕመናን መካከል በተፈጠረ ግጭት የሰዉ ህይወት ማለፉና የተጎዳ መኖሩንም ወኪላችን ጠቅሶልናል። የፖሊስ ጥበቃ መጠናከሩም ተሰምቷል።

https://p.dw.com/p/17EN9
Muslime feiern das Ende des Ramadans im Nationalstadium von Addis Abeba, Äthiopien Copyright: Getachew Tedla/DW, 19.08.2012, Addis Abeba, Äthiopien
Äthiopien Eid al Fitrምስል DW/Tedla Getachew

በሌላ በኩል የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የጋዜጣ አምደኛ ርዕዮት ዓለሙን የይግባኝ አቤቱታ ዛሬ ተመልክቷል። ለዉሳኔም ቀጠሮ ሰጥቷል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአራት ኪሎዉ ግቢ በተማሪዎች መካከል የተነሳዉ ግጭት ዛሬ የሰከነ ቢመስልም የመማር ማስተማሩ ሂደት አልተጀመረም። የሽብር ተግባር ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ አስራ አምስት ሰዎች በክትትል መያዛቸዉን ዘገባዎች ያመለክታሉ። በነዚህ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔርን በስልክ አነጋሬዋለሁ።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ