1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሁለቱ ሱዳን መንግሥታት ድርድር

ረቡዕ፣ ግንቦት 29 2004

የሱዳን እና የደቡብ ሱዳን መንግሥታት ዋነኛ ተደራዳሪዎች በሀገሮቻቸው መካከል የቀጠለውን ውጊያ ለማብቃትና አሁንም እያወዛገቡዋቸው ላሉ ጥያቄዎች መልስ ለማፈላለግ ካለፈው ሣምንት ወዲህ እንደገና በአዲስ አበባ በዝግ ስብሰባ ድርድር በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/159LO
An oil worker turns a spigot at an oil processing facility in Palouge oil field in Upper Nile state February 21, 2012, following a dispute with Sudan over transit fees. South Sudan will refuse do to any business in the future with oil trader Trafigura if it is proven that the firm bought oil from neighbouring Sudan in the knowledge that the cargo was seized southern crude, its oil minister told Reuters. Picture taken February 21, 2012. REUTERS/Hereward Holland (SOUTH SUDAN - Tags: ENERGY POLITICS BUSINESS)
ምስል Reuters

ሁለቱ ተቀናቃኝ ወገኖች ባለፈው ወር ወደ ጦርነት አፋፍ እንዳያደርሳቸው አስግቶ የነበረ ግጭት ካካሄዱ ወዲህ ፊት ለፊት ተገናኝተው ሲወያዩ ይህ የመጀመሪያቸው ቢሆንም፡ እስካሁን አንድም ስምምነት ላይ ለመድረስ አልቻሉም። ድርድሩ ለምን ወደፊት መራመድ ተሳነው? በለንደን የሚገኘውን እና ቻታም ሀውስ በመባል የሚታወቀውን የዓለም አቀፍ የፖለቲካ ጉዳዮች ተመልካች ተቋም የአፍሪቃ ክፍል ምክትል ተመራማሪ የፖለቲካ ተንታኝ ወይዘሮ አጂዋ አኒማዱ አስተያት ሰጥተዋል።

በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን መካከል የተጀመረው ድርድር ውጤት አልባ መሆኑን የሁለቱም ሀገሮች ባለሥልጣናት ቢያመለክቱም፡ በድርድሩ ስምምነት ሊደረስ ይችላል በሚል ተስፋ ውይይቱን እንደማያቋርጡ የሱዳን ተዳራዳሪ ኢድሪስ መሀመድ አብደል ቃዲር እና የደቡብ ሱዳን አቻቸው ፓጋን አሙም አስታውቀዋል። የአፍሪቃ ህብረት ባቋቋመው የሸምጋዮች ቡድን መሪ በቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት ታቦ ምቤኪ ሸምጋይነት የሚካሄደው የሁለቱ ሀገሮች ውይይት ለምን ይህን ያህል ጊዜ እንደወሰደበ በለንደን የሚገኙት ቻታም ሀውስ በመባል የሚታወቀው የዓለም አቀፍ የፖለቲካ ጉዳዮች ተመልካች ተቋም የአፍሪቃ ክፍል ምክትል ተመራማሪ የፖለቲካ ተንታኝ ወይዘሮ አጂዋ አኒማዱ ሲያስረዱ፡
« በሁለቱ መንግሥታት መካከል ለብዙ ጊዜ የኖረው፡ እንዲሁም፡ ደቡብ ሱዳን ባለፈው ሐምሌ ነፃ መንግሥት በሆነችበትም ጊዜ እንኳን በደቡብ ሱዳን እና በሱዳን ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ መሪዎች መካከል የቆየው የጥላቻ ታሪክ ይመስለኛል ምክንያቱ። ደቡቡ በሰሜኑ መንግሥት ተግልሎ ቆይቶዋል። እና አሁን ነጻ መንግሥት በመሆኑ እና ብዙ ሊነሱ የሚገባቸው ጉዳዮች በመኖራቸው ውይይቱን የማራዘሙን ጨዋታ ለመጫወት የፈለገ ይመስለኛል። »
ወይዘሮ አኒማዱ እንዳስረዱት፡ ለድርድሩ መጓተት ምክንያት ከሆኑትና ሁለቱን ተቀናቃኝ ወገኖች አሁንም ከሚያወዛግቡዋቸው ጉዳዮች መካከል ዋነኛው ሁለቱ ወገኖች እአአ በ 2005 ዓም በተፈራረሙት አጠቃላዩ የሰላም ስምምነት ውስጥ የተካተቱትና ደቡብ ሱዳን ነፃ መንግሥት ታቋቁም አታቋቁም በሚለው ጥያቄ ላይ ሕዝበ ውሳኔ ከማካሄድዋ በፊት መልስ ማግኘት የነበረባቸው ጉዳዮች እስካሁን መልስ አለማግኘታቸው ነው። ሰፊ ክርክር ካስነሱት ጉዳዮች መካከል፡ በሰሜንና በደቡብ ሱዳን መካከል ያለው ድንበር የሚካለልበት፡ የነዳጅ ዘይቱ ገቢ ክፍፍል፡ በሰሜን የሚኖሩት ደቡብ ሱዳናውያን እና በደቡቡ ሱዳን የሚኖሩ የሱዳን ተወላጆች ዜግነትን የተመለከቱት ጉዳዮች ይጠቀሳሉ። በተለይ የነዳጅ ዘይቱ ክፍፍል ጥያቄ መፍትሄ ያላገኘበት ድርጊት በነዳጅ ዘይቱ ገቢ ላይ ጥገኛ በሆነው በደቡብ ሱዳን መንግሥት ኤኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳርፍ ተገልጸዋል። ሆኖም ግን፣ አጂዋ አኒማዱ፣ ድርድሩ አለመቋረጡን አበረታቺ ሂደት ሆኖ ያዩታል።
« ይህ ውይይት መካሄዱ ራሱ አዎንታዊ ምልክት ነው ብየ አስባለሁ። እርግጥ፣ ሊመከርባቸው የሚገቡ ቡዙ ጉዳዮች በመኖራቸው ውይይቱ ሊራዘም ይችል ይሆናል። ግን ግልጽ በሆነ መንገድ እስከተመከረባቸውና ወደመፍትሔ እስከተደረሰ፣ ይህ ሁለቱ ሀገሮች ወደፊት እተወሳሰበ ሁኔታ ውስጥ የማይገቡበትን አዎንታዊ ሂደት ያመቻቻል ብየ አምናለሁ። »
በሱዳን መንግሥትና በሱዳን ሕዝብ ነጻ አውጪ ንቅናቄ መካከል ከሀያ ዓመት በላይ የቀጠለው ጦርነት እአአ በ 2005 ዓም ባበቃበት ስምምነት መደረስ ላይ እና ደቡብ ሱዳንም ነጻ መንግሥት በሆነችበት ድርጊት ላይ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትልቅ ሚና መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን፡ በዚያን ጊዜ ምንም እንኳን የፖለቲካ ተንታኣኝ አወዛጋቢ ጉዳዮች ሁሉ መፍትሄ ሳያገኙ በፊት ደቡብ ሱዳንን ነፃ የምትሆንበት ድርጊት አደገኟ እንደሚሆን ቢያስጠነቅቁም፡ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሰላሙ ስምምነት መፈረም የሁለቱ ወገኖች ችግር በጠቅላላ ያበቃል የሚል ተስፋ አሳድሮ ነበር፤ ያ ተስፋው እውን አልሆነም። በመሆኑም ሁለቱን ሀገሮች ለማቀራረብ አሁንም ጥረቱን እንደቀጠለ ይገኛል። ግ ው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ወደፊት መራመድ የተሳነው የአዲስ አበባው ውይይት ባፋጣኝ ውጤታማ እንዲሆን ድርሻ ሊይዝ ይችላል ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።
« ዓለም አቀፉ ግፊት በሁለቱም በኩል የሚያስገኘው ፋይዳ ይኖራል ብዬ አላስብም። ይህን በመሰለ ሁኔታ ወቅት፡ ውጥረቱ እንዲረግብና በሱዳንና በደቡብ ሱዳን የነዳጅ ዘይት ጥቅም ጭምር ሰበብ የተፈጠረው ውዝግብ እንዲያበቃ የሚፈልጉት ወገኖች ሁሉ ሰላማዊ መፍትሔ የሚገኝበትን ሀሳብ እንደሚደግፉ በግልጽ ካሳዩ፣ ያኔ ለውጥ ሊገኝ ይችላል። ለሁለቱ መንግሥታት ሰላማዊ የወደፊት ሁኔታ ማመቻቸት የሚቻልበት ስራ እንዲሰራ ከተፈለገ ግን፣ ይህ ውይይት ተጨባጭ ድምዳሜ ላይ እንዲደርስ ጊዜ መስጠት አስፈላጊ ይሆናል። »

A SPLA-N fighter sits with an anti-aircraft weapon near Jebel Kwo village in the rebel-held territory of the Nuba Mountains in South Kordofan, May 2, 2012. REUTERS/Goran Tomasevic (SUDAN - Tags: CIVIL UNREST)
ምስል Reuters
ARCHIV - Südafrikas Präsident Thabo Mbeki während einer Tagung in Pretoria (Archivfoto vom 03.04.2008). Südafrikas Präsident Thabo Mbeki trat am 21.09.2008 zurück. Seine Parteiführung vom Afrikanischen Nationalkongress (ANC) hatte ihn am 20. September dazu aufgefordert. Mbeki war im November 2007 beim Kampf um den ANC-Vorsitz unterlegen. EPA/JON HRUSA (zu dpa-Paket: "Jahreswechsel" vom 03.12.2008) +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture-alliance/ dpa

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ