1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሁለቱ ሱዳኖች ስምምነት

ሐሙስ፣ መስከረም 17 2005

ሁለቱ ወገኖች ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በተፈራረሙት ስምምነት መሰረት የተቋረጠው ወሳኙ የነዳጅ ዘይት ምርትና ሽያጭ ይቀጥላል ። የደረሱበት ስምምነት ደቡብ ሱዳን በሱዳኑ የቀይ ባህር ወደብ በኩል ነዳጅ ዘይት ለውጭ ገበያ ማቅረብ ያስችላታል ።

https://p.dw.com/p/16GeU
(FILE) A file picture dated 19 January 2010 shows Sudanese President Omar el Bashir (R) and First Vice President and President of the Government of Southern Sudan, Salva Kiir Mayardit (L), participating in celebrations marking the 5th anniversary of the signing of the Comprehensive Peace Agreement (CPA) in Yambio, Sudan. Omar el Bashir has won the country's first multiparty elections in 24 years, election officials said on 26 April 2010. The polls are supposed to usher in a new era of democracy in Sudan, which is recovering from a decades-long civil war between the north and south. EPA/TIM MCKULKA - UNMIS - HANDOUT EDITORIAL USE ONLY/NO SALES +++(c) dpa - Bildfunk+++
አል በሽርና ኪርምስል picture-alliance/dpa


4 ቀናት አዲስ አበባ ውስጥ የተደራደሩት ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ወሰናቸውን ለማስጠበቅና የነዳጅ ዘይት ምርትና ንግድን ለመቀጠል የሚያስችል ስምምነት ዛሬ ተፈራረሙ ። የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሽርና የደቡብ ሱዳኑ አቻቸው ሳልቫ ኪየር የትብብር ስምምነት ፣ እንዲሁም የሁለቱ ሃገራት የመከላከያ ሚኒስትሮች ደግሞ በወሰናቸው ላይ ከጦር እንቅስቃሴ ነፃ የሆነ ቀጣና ለመከለል የሚያስችል ስምምነት ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ተፈራርመዋል ። ሁለቱ ወገኖች ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በተፈራረሙት ስምምነት መሰረት የተቋረጠው ወሳኙ የነዳጅ ዘይት ምርትና ሽያጭ ይቀጥላል ። የደረሱበት ስምምነት ደቡብ ሱዳን በሱዳኑ የቀይ ባህር ወደብ በኩል ነዳጅ ዘይት ለውጭ ገበያ ማቅረብ ያስችላታል ። ሆኖም በአሁኑ ድርድር ደቡብ ሱዳን ከሱዳን ነፃ በወጣችበት ወቅት ያልተፈቱ የአብዮ ግዛትን ጨምሮ ሌሎች አወዛጋቢ ጉዳዮች መፍትሄ አላገኙም ። ሁለቱ ሱዳኖች ስምምነት የተፈራረሙት የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ልዩነቶቻቸውን እንዲያስወግዱ ለሶስተኛ ጊዜ ያሰቀመጠው የጊዜ ገደብ ዛሬ ሊያበቃ ሲል ነው ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ