1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሂውማን ራይትስ ዎች ዘገባ እና የኢትዮጵያ አስተያየት

ረቡዕ፣ ጥቅምት 10 2003

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች የኢትዮጵያ መንግስት ከለጋሽ ሀገሮች የሚያገኘውን የልማት ርዳታ ህዝቡን ለመጨቆን ይጠቀምበታል ሲል በመክሰስ ያወጣው ጽሁፍ ሚዛናዊ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ቃል አቀባይ አቶ ብርሀኑ አባዲ ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/Pipa

የመንግስት ተቃዋሚዎች የዚሁ ርዳታ ተጠቃሚ እንደማይሆኑ ያስታወቀው ሂውማን ራይትስ ዎች ለጋሽ ሀገሮች ለኢትዮጵያ በሚሰጡት ርዳታ ላይ አስፈላጊውን ምርመራ እና ክትትል እንዲያደርጉ በዘገባው መጠየቁ የሚታወስ ነው።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ
ተክሌ የኋላ