ሰኞ፣ ሚያዝያ 2 2009
ማስታወቂያ
ከአዲስ አበባ በ150 ክሎሜትር ክልል ዉስጥ ያለዉ የማህበረሰቡ እንቅስቃሴ በትምህርት፣ በጤና በሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች መተሳሰሩ እየጨመረ ስለ መጣ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት «በፊት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት አከባብ የነበረዉን አሁን በከፊል እስከ 2:30 እንድያገለግሉ መደረጋቸዉን» አቶ ተስፋዬ ይናገራሉ።
በአገሪቱ የህብረተሰቡ እንቅስቃሴ ኢየጨመረ ስለመጣም የማታ ትራስንፖርት አገልግሎት ቀስ በቀስ ተፈጻሚ ለማድረግ ማቀዱ አቶ ተስፋዬ ያስረዳሉ። አቶ ተስፋዬ በለስልጣኑ ከዚህ ቀደም ማታ በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ የሰዓት ገደብ ያስቀመጠበትን ዋና ዋና ምክንያቶችም አሉ ይላሉ።
ከዚህ ቀደም የአባይ ትራንስፖርት ቦርድ ሊቀመንበር ነበርኩ ያሉንና የስድስት አዉቶብስ ባለንብረት መሆናቸዉን የሚናገሩት አቶ መለሰ ክሸን የማታ ትራንስፖርትን የመፍቀድ እቅድ ለአገሪቱ ኤኮኖሚ ጠቀሜታ አለዉ ይላሉ።
በቂ መሰረተ ልማት የለለበት፣ ማለትም የመንገድና የማብራት፣ እንዲሁም ከፍተኛ የደህንነት ችግር ያለበት አገር ዉጥ ባለስልጣኑ ማታ ላይ ተሽከርካርዎች እንዲንቀሳቀሱ ማቀዱ ተጽዕኖ እንዳለዉ የሚናገሩ አልጠፉም።
ላለፉት ጊዜያት ባለስልጣኑ በህገወጥ መንገድ ማታ ተሽከርካሪ የሚያሽከረክሩትን መቆጣጠር ቢሞክርም ጉዳዩ አስቸጋሪ ሆኖ መቀጠሉንም ዘገባዎች ይጠቁማሉ።
መርጋ ዮናስ
ኂሩት መለሰ