1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሹ ድርድር ውጤት

ሰኞ፣ ጥቅምት 10 2007

ኢትዮጵያ ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ባለው በትልቁ የህዳሴ ግድብ ሰበብ የተፈጠረውን ልዩነት ለማጥበብ የኢትዮጵያ ፣የግብፅ እና የሱዳን ተወካዮች እና ባለሙያዎች ባለፈው ሐሙስ እና ዓርብ ካይሮ ውስጥ የሶስትዮሽ ውይይት አካሄዱ።

https://p.dw.com/p/1DYqu
Nil Dammbau in Äthiopien Archiv 28.05.2013
ምስል William Lloyd-George/AFP/Getty Images

የግድቡ ግንባታ ያስነሳውን ውዝግብ በውይይት የተነሱት አጀንዳዎች፣ የድርድሩ ውጤቱ እና ቀጣይ ሂደትን ምን ይመስላል?

ሶስቱ ሀገራት ባለፈው መስከረም በካርቱም፣ ሱዳን ባካሄዱት ስብሰባ ላይ የግድቡ ግንባታ በዓባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው ትልቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ በታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ የሚያጠና አንድ ዓለም አቀፍ ኮሚቴ ማቋቋማቸው ይታወሳል። ኮሚቴው ከተቋቋመ ወዲህም ሶስቱ ሀገራት ተገናኝተው ምክክር ሲያደርጉ ያለፈው ሳምንቱ የመጀመሪያ ጊዜያቸው ነበር። ከኢትዮጵያ 10 ያህል ልዑካንን ይዞ ወደ ካይሮ የተጓዘው ቡድን ከሁለቱ ሀገራት ጋር በአራት አጀንዳዎች ላይ መወያየቱን በውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የወሰን እና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ተሾመ አጥናፌ ገልጸውልናል።

በዚህ ስብሰባ ፤ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ሰባት ዓለም አቀፍ አማካሪዎች ተመርጠዋል። በተጨማሪም የተደረሱትን ውጤቶች አቶ ተሾመ ለዶይቸ ቬለ ገልፀዋል።

Äthiopien Staudamm Nil 16.03.2014
ምስል Reuters

ለሁለት ሙሉ ቀናት በተካሄደው ስብሰባ ሶስቱም ሀገራት ባነሱዋቸው ጉዳዮች ላይ ስምምነት ቢደርሱም፣ ግብጽ የግድቡ ግንባታ ከወንዙ የምታገኘውን የውሃ ፍሰት ይቀንስብኛል በማለት አሁንም ስጋት እንዳላት ነው የምትገልጸው። ያም ቢሆን ግን ኢትዮጵያ በጀመረችው እና አሁን ወደ 40 በመቶ ያህሉ የተጠናቀቀውን የህዳሴ ግድብ ግንባታን እንደምትቀጥልበት አስታውቃለች። የአሁኑ የሶስትዮሽ ድርድር በዚሁ የኢትዮጵያ አቋም ላይ ሳይሆን፣ በተለይ የግድቡ ግንባታ ሊያስከትላቸው በሚችላቸው ማህበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ተፅዕኖ ላይ በይበልጥ ያረኮረ ነበር አቶ ተሾመ እንዳስረዱት።

በትልቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ላይ የተጀመረው የሶስትዮሹን ውይይት ሂደትን በተመለከተ የኢትዮጵያ፣ የግብፅ እና የሱዳን ተወካዮች ከአንድ ወር ከ 10 ቀን በኋላ ካርቱም ላይ ለግምገማ ስብሰባ ይገናኛሉ።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ