1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የለንደኖቹ የባርነት ሰለባዎች

ዓርብ፣ ኅዳር 13 2006

ደቡብ ለንደን ውስጥ ሶስት ሴቶች ከ 30 ዓመት በላይ ያለፍላጎታቸው በባርነት ከታገቱ በኋላ ትናንት ነፃ መሆናቸው ተሰምቷል።

https://p.dw.com/p/1AMhQ
ምስል BEN STANSALL/AFP/Getty Images

እነዚህ ሶስት ሴቶች ከተወሰኑ ጊዜያት በስተቀር ፍፁም ለ30 ዓመታት የውጩውን ዓለም አይተው እንደማያውቁ ነው የተገለፀው። ሴቶቹን በመኖሪያ ቤታቸው እንደ ባርያ በመያዝ የተጠረጠሩ አንድ ወንድና አንድ ሴት ይህን ድርጊት ተከትሎ ከታሰሩ በኋላ አሁን በዋስ መለቀቃቸውን ፖሊስ አስታውቋል። ያለፍቃዳቸው በባርነት ታግተው ስለነበሩት ሶስት ሴቶች ማንነት እና ያሉበት ሁኔታን በተመለከተ ከለንደን ዘገባ ደርሶናል።

ሀና ደምሴ

ሂሩት መለሰ