1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የለጋሽ ሀገሮች ስብሰባ በማድሪድ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 12 1996

ወደ ሰባ የሚጠጉ ሀገሮችና አሥራ ሰባት የመንግሥት ያልሆኑ ድርጅቶች በኢራቅ መልሶ ግንባታ ወጪ ላይ ለመመካከር በዛሬው ዕለት በስጳኝ መዲና ማድሪድ ስብሰባ ጀመሩ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ኮፊ አናን የከፈቱት የሁለቱ ቀን ምክክር አሜሪካውያኑ ለኢራቅ መልሶ ግንባታ የሚያስፈልገውን የፊናንስ ርዳታ በተመለከተ፡ አሜሪካውያኑ በዓለም አቀፉ ኅብረተ ሰብ ድጋፍ ላይ ሊተማመኑ መቻል አለመቻላቸው የሚፈተንበት የመጀመሪያው ሁነኛ አጋጣሚ ሆኖ ነው የ

https://p.dw.com/p/E0gC

��ታየው። ስብሰባው ለኢራቅ በርዳታ የሚቀርበውን ገንዘብ የማስተዳደሩንና የመቆጣጣሩን ጥያቄዎች በተለይ ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚወያይባቸው ነው የተገለፀው።

አስተናጋጅዋ ስጳኝ እና የዓለሙ መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ኮፊ አናን በስብሰባው አኳያ ብሩሑን አመለካከት ቢያንፀባርቁም፡ ጉባዔው ዓላማውን እንደማይመታ ታዛቢዎች ግምታቸውን ገልፀዋል። ለኢራቅ መልሶ ግንባታ እአአ እስከ 2007 ዓም ድረስ ሀምሣ አምስት ሚልያርድ ዶላር እንደሚያስፈልግ የተጠቀሰ ሲሆን፡ ከዚሁ የገንዘብ መጠን መካከል በማድሪዱ ስብሰባ ላይ ንዑሱ ከፊል ብቻ እንደሚገኝ ነው የሚጠበቀው።

ዩኤስ አሜሪካ ሀያ ሚልያርድ ዶላር ለመስጠት ቃል ገብታለች፤ ይሁንና፡ በሀገርዋ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ፍላጎት መሠረት፡ ግማሹ በብድር መልክ እንዲሰጥ ነው የተወሰነው። የዓለም ባንክና ጃፓን እያንዳንዳቸው አምስት ሚልያርድ ዶላር ለርዳታ ዝግጁ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። በአንፃራቸው፡ አሥራ አምስት ሀገሮች በአባልነት የሚጠቃለሉበት የአውሮጳ ኅብረት እአአ እስከ 2004 ዓም መጨረሳ ድረስ ሁለት መቶ ሠላሣ ሚልዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብቶዋል። ይህም በኢራቅ ዋነኛዋ የዩኤስ ተጓዳኝ ብሪታንያ ለመስጠት ከወሰነችው ግንዘብ መካከል አንድ አራተኛውን ያህል መሆኑ ነው። በመሆኑም፡ ለኢራቅ መልሶ ግንባታ መቅረብ አለበት ከተባለው ገንዘብ መካከል ቢያንስ ሀያ ሚልያርድ ተጓድሎ የሚገኝ ሲሆን፡ ይኸው ጉድለት በማድሪድ ስብሰባ ላይ የሚሟላበት ዕድል በፍፁም አልታየም።

በዚሁ ጉባዔ ላይ ከተሳኣተፉት ሀገሮች መካከል አንድ አምስተኛው በሚንስትሮች ደረጃ ብቻ መወከላቸው ሲታሰብ፡ ቀደም ሲል ሀገራቱ የደረሱዋቸውን ውሳኔዎች ይለወጣሉ ተብሎ አይጠበቅም። ተወካዮቹ ወደ ጉባዔው ፅኑ አቋም ይዘው የተጓዙ ሲሆን፡ በርዳታ የሚያቀርቡትን ገንዘብ መጠን፡ እስካሁን ይፋ ካላደረጉ፡ በግልፅ ለማሳወቅ ነው። ለምሳሌ ኩዌት በውጭ ጉዳይ ሚንስትርዋ አማካይነት እንዳስታወቀችው፡ ለኢራቅ የምትሰጠው ርዳታ ከፍ ያለ ነው። ጀርመን፡ ፈረንሣይና ሩስያን የመሳሰሉ ሀገሮ፧ች ደግሞ እስካሁን ለማድረግ ካገለፁት ትብብር ሌላ በስብሰባው አዲስ ሀሳብ እንደማይቀርቡ ነው ያስታወቁት። ከአውሮጷ ኅብረት በጀት አንድ አራተኛውን የምትሸፍነው ጀርመን የኢራቅን ፖሊሶች የማሠልጠኑን በመሳሰሉ ሌሎች በርካታ ፕሮዤዎች ውስጥ ቀጥተኛ ርዳታም ታደርጋለች። ባጠቃላይ፡ ለኢራቅ አንድ መቶ ሚልዮን ዶላር፡ (ስጳኝ ከምትሰጠው መካከል አንድ ሦስተኛው መሆኑ ነው፡) እንደምትሰጥ ነው ቃል የገባችው።

በማድሪድ ስብሰባ የተሳተፉት ተወካዮች ዛሬ በመጀመሪያው የጉባዔ ቀን በሥራ ቡድኖች ተከፋፍለው በኢራቅ ሰብዓዊ ጊዚያዊ ሁኔታ፡ በሰብዓዊ መብት ይዞታ፡ በፀጥታ ጥያቄዎች፡በድንበሩ እና በፍትሕ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ። በነገው ዕለት ደግሞ የኢራቅ አስተዳዳሪ እና ኢራቃውያኑ የጊዚያዊው የሽግግር ምክር ቤት አባላት በስብሰባው ንግግር ካሰሙ በኋላ፡ ከጉባዔው ተካፋዮች ጋር ተጨባጩ ዓለም አቀፍ ርዳታ በሚገኝበት ሁኔታ ላይ ይመክራሉ።