1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሊቢያና የኢጣሊያ ስምምነት

ሐሙስ፣ ግንቦት 11 2008

የዚህ ሳምንቱ ስብሰባ ወደሰሜን አዉሮጳ መሻገር የሚሹ ተሰዳጆች በሰሜን አፍሪቃ በተለይም ሊቢያን መሸጋገሪያ እያደረደረጉ በሕገወጥ መንገድ ወደጣሊያን መሻገራቸዉ የሚገታበትን መንገድም ለመቀየስ ያለመ ነዉ

https://p.dw.com/p/1IqmH
ምስል Reuters/H. Amara

[No title]

የኢጣሊያ መንግሥትና አዲስ የተመሠረተዉ የሊቢያ አንድነት መንግሥት ባለሥልጣናት ሥለ ሁለቱ ሐገራት ትብብር ተወያዩ። ቀደም ሲል ኢጣሊያን በሊቢያ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ፤ ሊቢያም በለዉጡ የኃይል አቅርቦት የምታደርግበትን ዉል ሁለቱ ሃገራት ተፈራርመዉ ነበር። የዚህ ሳምንቱ ስብሰባ ወደሰሜን አዉሮጳ መሻገር የሚሹ ተሰዳጆች በሰሜን አፍሪቃ በተለይም ሊቢያን መሸጋገሪያ እያደረደረጉ በሕገወጥ መንገድ ወደጣሊያን መሻገራቸዉ የሚገታበትን መንገድም ለመቀየስ ያለመ ነዉ። እንዲያም ሆኖ መረጋጋት ከራቃት ሊቢያ ጋር የታሰበዉ ተገባራዊነቱ እስከምን ድረስ ነዉ የሚለዉ ማነጋገሩ አልቀረም። ሸዋዬ ለገሠ የሮሙ ወኪላችን ተኽለእግዚ ገብረ ኢየሱስን ጉዳዩን በማንሳት በስልክ አነጋግራዋለች።

ተኽለእግዚ ገብረ ኢየሱስን

ሸዋዬ ለገሠ