1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሊቢያው ጦርነት እና የምዕራባውያኑ አቋም

ረቡዕ፣ መጋቢት 21 2003

የምዕራባውያኑ የጦር አውሮፕላኖች ሊቢያን ለ 11 ኛ ቀን ከአየር መደብደባቸውን በቀጥሉበት በዛሬው ዕለት የሊቢያው መሪ የሞአመር ጋዳፊ ኃይሎች ፣ አማፅያንን ከአንዳንድ ቁልፍ ከተሞች ማስለቀቃቸው ተሰምቷል ።

https://p.dw.com/p/RDz7
የለንደኑ ጉባኤ ተሳታፊዎችምስል AP

ከሊቢያ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት አማፅያኑ ነዳጅ ዘይት ከሚጣራበት የራስ ላኑፍ ከተማ አፈግፍገዋል ። በሞአመር ጋዳፊ ኃይሎች ከባድ ጥቃት ፣ ግስጋሴያቸው የተገታውን የጋዳፊን ተቃዋሚዎች የማስታጠቁ ጉዳይ ኃያላኑን መንግስታት ማወዛገቡን ቀጥሏል ። ትናንት በሊቢያ ጉዳይ ለንደን ውስጥ የተካሄደው ጉባኤ ደግሞ ጋዳፊ ሀገሪቱን ለቀው እንደወጡ ሲስማማ በሚወጡበት ሁኔታ ላይ ግን አንድ አቋም መያዝ ተስኖታል ።

NO FLASH Libyen Einsatz Tripolis
ትሪፖሊ አቅራቢያ የተካሄደ ድብደባምስል AP

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ