1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሊቢያ ምክር ቤታዊ ምርጫ ውጤት

ሐሙስ፣ ሐምሌ 12 2004

በሊቢያ የቀድሞው የሽግግሩ ምክር ቤት መሪ ማህሙድ ጂብሪል የሚመሩት ለዘብተኛው የተባበሩት ኃይላት ህብረት ከሁለት ሣምንት በፊት የተካሄደው ምክር ቤታዊ ምርጫ አሸናፊ ሆነ።

https://p.dw.com/p/15b9z
Der Vorsitzende des Exekutivrates des Nationalen Uebergangsrates Libyens, Mahmud Dschibril, spricht am Donnerstag (30.06.11) in Berlin im Auswaertigen Amt auf einer Pressekonferenz. Mittelpunkt der Gespraeche mit dem deutschen Ausseniminster war die aktuelle Lage in Libyen. Foto: Patrick Sinkel/dapd
የተባበሩት ኃይላት ህብረት መሪ ማህሙድ ጂብሪልምስል dapd

በጎረቤት ቱኒዝያ እና ግብፅ እንደሆነው በሊቢያም ያሸንፍ ይሆናል ተብሎ የነበረው የሙሥሊም ወንድማማችነት ፓርቲ ያቋቋሙት የፍትህ እና የመልሶ ግንባታ ፓርቲ በምርጫው ሁለተኛነቱን ቦታ ብቻ ነው የያዘው። የተቀሩት እና አብላጫ የሆኑት 120 መንበሮች በነፃ ለሚወዳደሩ ዕጩዎች የተመደቡ በመሆናቸው፡ የትኛው ወገን አብላጫ ድምፅ እንደሚኖረው እስካሁን በግልጽ አልታወቀም።

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ