1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሊቢያ ቀዉስና መፍትሔዉ

ረቡዕ፣ ግንቦት 16 2009

የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮ ፌደሪካ ሞጎሮኒ የመሩት ሥብሰባ የሊቢያ ተፋላሚ ኃይላት ያደረጉት ሥምምነት ገቢራዊነትን ገምግሟል።ለገቢራዊነቱ ሥለሚያስፈልገዉ ድጋፍና ርዳታም መክሯል።

https://p.dw.com/p/2dWy6
Symbolbild Wahabismus- Wahabi Muslime gegen Moamer Kadhafi in Libyen
ምስል AFP/Getty Images

(Beri.Brussels) Libyen krise-Quartet - MP3-Stereo

 

የሊቢያን ቀዉስ ለማስወገድ በጋራ «እንጥራለን» የሚሉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፤የአዉሮጳ ሕብረት፤ የአፍሪቃ ሕብረት እና የአረብ ሊግ ተወካዮች ትናንት ብራስልስ-ቤልጂግ ዉስጥ ተሰብስበዉ ነበር።የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮ ፌደሪካ ሞጎሮኒ የመሩት ሥብሰባ የሊቢያ ተፋላሚ ኃይላት ያደረጉት ሥምምነት ገቢራዊነትን ገምግሟል።ለገቢራዊነቱ ሥለሚያስፈልገዉ ድጋፍና ርዳታም መክሯል።አራትዮሽ ተብሎ የሚጠራዉ ስብስብ የመጀመሪያ ስብሰባዉን ባለፈዉ መጋቢት ካይሮ ዉስጥ ያደረገ ሲሆን ሰወስተኛዉን አዲስ አበባ ለማድረግ ቀጠሮ ይዟል።የቀድሞ የሊቢያ አማፂያን በሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) የጦር ድጋፍ የቀድሞዉን የሊቢያ ሥራዓት ካፈራረሱ ወዲሕ ሰሜን አፍሪቃዊቱ ሐገር የሥራዓተ-አልበኞች መፈንጫ ሆናለች።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ