1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሊቢያ የርዳታ መርከብና እስራኤል

ረቡዕ፣ ሐምሌ 7 2002

የእስራኤል ጦር ባለፈዉ ወር እርዳታ የጫነች መርከብን ወርሮ የቱርክ ዜጎችና ተወላጆችን በመግደሉ ሰበብ የተነሳዉ የሁለቱ ሐገሮች ዉዝግብ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ።

https://p.dw.com/p/OJEx
የፍልስጤሙ ወጣት-የርዳታ ላኪዉን ፎቶ ይዞምስል AP

እስራኤል በጣለችዉ እገዳ ምክንያት ለተቸገረዉ የጋዛ ሕዝብ የዕርዳታ እሕልና መድሐኒት ለማድረስ ተጉዛ የነበረችዉ የሊቢያ መርክብ አቅጣጫዋን እንድትቀር የእስራኤል ባሕር ሐይል አስገደዳት። መርከቢቱ ከግሪክ ወደ ጋዛ መቅዘፍ የጀመረችዉ ባለፈዉ ቅዳሜ ነበር።የእስራኤል ጦር የመርከብቱን ጉዞ ሚሳዬል በደገኑ የጦር ጀልባዎች ሲያደናቅፍ ነበር።መርከቧ ዛሬ ማርፈጃዉ ላይ አቅጣጫዋን ቀይራ ወደ ግብፅ ወደብ ለመቅዘፍ ተገድዳለች።ይሕ በንዲሕ እንዳለ የእስራኤል ጦር ባለፈዉ ወር እርዳታ የጫነች መርከብን ወርሮ የቱርክ ዜጎችና ተወላጆችን በመግደሉ ሰበብ የተነሳዉ የሁለቱ ሐገሮች ዉዝግብ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ።የጂዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ነብዩ ሲራክ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ