1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሊቢያ ፀጥታና አዲሱ መንግሥቷ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 9 2008

የዩናይትድ ስቴትሱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር እንዳሉት ተሰብሳቢዎቹ አዲሱን የሊቢያ መንግሥት ለማስታጠቅና ለመርዳት ተስማምተዋል።---በምዕራባዉያን መንግሥታት ጦር የተደገፉት የቀድሞዎቹ የሊቢያ አማፂያን የሐገሪቱን የረጅም ጊዜ መሪ ኮሎኔል ሙዓመር ጋዳፊን ከገደሉ ወዲሕ ሰሜን አፍሪቃዊቱ ሐብታም ሐገር የፍርስራሽ መከመሪያ እንደሆነች አምስተኛ ዓመቷ

https://p.dw.com/p/1IpFT
ምስል Getty Images/L.Foeger

በምዕራባዉያን መንግሥታት ድጋፍና ግፊት ለተመሠረተዉ ለአዲሱ የሊቢያ ጊዚያዊ ብሔራዊ አንድነት መንግሥት የጦር መሳሪያ እንደሚያስታጥቁ ዩናይትድ ስቴትስና ተባባሪዎችዋ አስታወቁ።ትናንት ቪየና-ኦስትሪያ ዉስጥ ሥለ ሊቢያ የተነጋገረዉ ሥብሰባ ሲያበቃ የዩናይትድ ስቴትሱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር እንዳሉት ተሰብሳቢዎቹ አዲሱን የሊቢያ መንግሥት ለማስታጠቅና ለመርዳት ተስማምተዋል።በሊቢያ ላይ የተጣለዉ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ግን ገና አልተሰነሳም።በምዕራባዉያን መንግሥታት ጦር የተደገፉት የቀድሞዎቹ የሊቢያ አማፂያን የሐገሪቱን የረጅም ጊዜ መሪ ኮሎኔል ሙዓመር ጋዳፊን ከገደሉ ወዲሕ ሰሜን አፍሪቃዊቱ ሐብታም ሐገር የፍርስራሽ መከመሪያ እንደሆነች አምስተኛ ዓመቷ።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ