1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሊባኖሥ መንግሥት መመስረት ትርጉሙ

ረቡዕ፣ ኅዳር 2 2002

የፖለቲካ ታዛቢዎች እንደሚሉት የሊባኖስ ፖለቲከኞች ስምምነት ኢራንና ሶሪያ ባንድ ወገን ሳዑዲ አረቢያ በሌላ ወገን ሆነዉ የሚያደርጉት መጓተት የማብቃቱ ምልክት ነዉ

https://p.dw.com/p/KU5C
ሐሪሪና ነስረላሕምስል AP

አምስት ወራት ያወዛገበዉ የሊባኖስ ምርጫ ዉጤት በሰላም ዉል አበቃ።ባለፈዉ ሰኔ በተደረገዉ ምርጫ አብላጭ ድምፅ ያገኘዉ ለዘብተኛዉ የሱኒዎች የፖለቲካ ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በመተባበር ከትናንት በስቲያ ብሔራዊ የአንድነት መንግሥት መሥርቷል።የሊባኖስ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች ዉዝግባቸዉን በሰላማዊ ድርድር በማስወገዳቸዉ የአዉሮጳ ሕብረትና የተለያዩ ምዕራባዉያን ሐገራት ድጋፍ ደስታቸዉን እየገለጡላቸዉ ነዉ።የፖለቲካ ታዛቢዎች እንደሚሉት የሊባኖስ ፖለቲከኞች ስምምነት ኢራንና ሶሪያ ባንድ ወገን ሳዑዲ አረቢያ በሌላ ወገን ሆነዉ የሚያደርጉት መጓተት የማብቃቱ ምልክት ነዉ።የጂዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ነብዩ ሲራክ

ነጋሽ መሐመድr

አርያም ተክሌ