1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የላስ ቬጋስ ጥቃት

ሰኞ፣ መስከረም 22 2010

በአሜሪካዋ ላስ ቬጋስ ከተማ አንድ ታጣቂ በሙዚቃ አፍቃሪዎች ላይ በከፈተው ተኩስ ቢያንስ 58 ሰዎች ገድሎ ከ200 በላይ አቆሰለ። የእሩምታ ተኩሱ ያደረሰው ጉዳት አሜሪካ በዘመናዊ ታሪኳ አይታው የማታውቀው ነው ተብሏል። ባለሥልጣናት ተጠርጣሪው ታጣቂ ስቴፈን ፓዶክ የተባለ የ64 አመት ነጭ ሽማግሌ ነው ብለዋል።

https://p.dw.com/p/2l7bl
Las Vegas Schießerei
ምስል Getty Images/D.Becker

ቢያንስ 50 ሰዎች የገደለው ጥቃት በአሜሪካ 

ማንዳላይ ቤይ ከተባለው ሆቴል ላይ ሆኖ የኅገረሰብ ሙዚቃ ዝግጅት ታዳሚያን ላይ ተኩስ የከፈተው ግለሰብ መገደሉን ፖሊስ አረጋግጧል። ራሱን "እስላማዊ መንግሥት" ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስዷል። ታጣቂ ቡድኑ ጥቃቱ የተፈጸመው ከበርካታ ወራት በፊት ኃይማኖቱን ወደ እስልምና በቀየረ ወታደር የተፈጸመ ነው ብሏል። ስለጥቃቱ የአሜሪካው ወኪላችን መክብብ ሸዋን ወደ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት አነጋግሬዋለሁ።


መክብብ ሸዋ
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ