1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የልጆችን ቁጥር መመጠን

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 24 2004

አንዱን የዓለም ክፍል የህዝብ ቁጥር መብዛት፤ የጥሬ ሃብቶች ማነስና የመሬት ጥበት ሲያሳስበዉ፤ በሌላዉ ደግሞ የህዝብ ቁጥር እንዳይመናመን ቤተሰቦች ትዉልድ እንዲተኩ ይበረታታሉ። የህዝብን ቁጥር ለመቀነስ የልጆችን ቁጥር መመጠን እየተባለ ነዉ።

https://p.dw.com/p/15hKe
ምስል Oliver Ramme

ለምሳሌ ሩዋንዳ ለቆዳ ስፋቴ አይመጥንም ያለችዉን የህዝብ ቁጥር እድገት ለመገደብ የቤተሰብ እቅድ መርሆ ከነደፈች ዓመታት ተቆጥረዋል። ህግ ሆኖ መዉጣቱ ባይገለፅም የዛሬ አምስት ዓመት ነዉ ሩዋንዳ አንድ ቤተሰብ ከሶስት ልጅ በላይ እንዳይወልድ የሚደነግገዉን መርሆ ያረቀቀችዉ። የህዝብ ቁጥርን ለመመጠን እንዲህ ያለዉን የቤተሰብ ምጣኔ ረቂቅ በመቅረፅ ሩዋንዳ የመጀመሪዋ አፍሪቃዊት ሀገር መሆኗ ተገልጿል።

Yasmin Antibabypille
ምስል Bayer Schering Pharma AG / Matthias Lindner

ሩዋንዳ ዉስጥ በጎርጎሮሳዊዉ የዘመን ቀመር 1994ዓ,ም የተካሄደዉ እና በሰዉ ዘር እልቂት የሚጠቀሰዉ የጥፋት ርምጃ የህዝቡን ቁጥር ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን ሀብት አድቅቆ ማለፉ አይዘነጋም። እንዲያም ሆኖ ግን ከዚህ ወቅት በኋላ ሩዋንዳ በተለያዩ ዘርፎች መሻሻል ለማምጣት መጣሯ ይነገርላታል። የህዝብ ቁጥር መጨመር እና በጤናዉ ዘርፍ ያለዉ የአገልግሎት ስልት ዉሱንነት ግን ዘላቂ ልማትን ለማጠናከር ለሚደረገዉ ጥረት በእንቅፋነት ይጠቀሳሉ። ሩዋንዳ አፍሪቃ ዉስጥ ከሚገኙ የቆዳ ስፋታቸዉ አነስተኛ ከሆኑ ሀገሮች አንዷ ናት። በአንድ ስኩየር ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ ከአራት መቶ በላይ ሰዎች እንደሚኖሩ ነዉ የሚገለፀዉ።

Learning by Ear - Family Planning
ምስል LAI F

ይህን ያስተዋለዉ የሩዋንዳ መንግስት አንድ ቤተሰብ ከሶስት ልጅ በላይ እንዳይወልድ የሚደነግገዉን መርሆ ካረቀቀ አምስት ዓመታት ተቆጥረዋል።አሁን መንግስት ህዝቡን ለማሳወቅ ያደረገዉ ጥረት ፍሬ አፍርቷል ባይ ነዉ። አንዳንድ ቤተሰቦች ከአምስት እና ስድስት ልጅ በላይ ወልደን ለማሳደግ አቅማችን አልችልም በማለት የወሊድ መከላከያ ስልቶችን ለመጠቀም መቁረጣቸዉን ይገልፃሉ። በተቃራኒዉ የዘር ማጥፋቱ ርምጃ ዘር ማንዘራችንን አሳጥቶናል የሚሉ ዜጎች ደግሞ በርካታ ልጆችን ለመዉለድ እንደሚሹ በይፋ ይናገራሉ። ከዓለም ለዚህ ርምጃ በአርአያነት የሚታየዉ የቻይናዉ አንድ ልጅ በአንድ ቤተሰብ መርህ ነዉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ