የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተሸለሙ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 13 2004ማስታወቂያ
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር በላይ ካሳ ሳሳካዋ አፍሪቃን አሶሲየሽን ከተባለ ድርጅት መሸለማቸው ታወቀ። ፕሬፌሰሩ ለሽልማት የበቁት ድርጅቱ ከሚንቀሳቀስባቸው የአፍሪቃ ሀገራት ተወዳድረው በተለይም የግብርና ልማት ሰራተኞችን አቅም በማጎልበት ላበረከቱት አስተዋፅኦ እንደሆነም ተጠቅሷል። በሽልማቱ የላቀ ዘላቂ የአስተዳደር ሜዳይ እና የ100 ሺህ ብር ለማግኘት በቅተዋል ሲል የድሬዳዋው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር በዘገባው ገልጿል።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ