1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሐረር ቢራ ሠራተኞች የረሀብ አድማ

ሰኞ፣ ግንቦት 5 2005

የሐረር ቢራ የጥበቃ ሠራተኞች ከስራ ገበታችን ላይ ያለአግባብ ተፈናቀልን በሚል የረሀብ አድማ ማድረጋቸው ታወቀ። ሠራተኞቹ መፍትሄ ካላገኙ የሰራተኞቹ ማኅበር ቀጣይ ርምጃዎችን እንደሚያከናውን ዝቷል።

https://p.dw.com/p/18X6U
ምስል picture-alliance/dpa

ቁጥራቸው ወደ  80 የሚጠጋ የሐረር ቢራ የጥበቃ ሠራተኞች የረሀብ አድማ አደረጉ። የኅብረት ስምምነቱ  የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ እንዲሁም የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ  ስምምነትን በጣሰ መልኩ ድንገት ከስራ ስላባረረን ከቤተሰቦቻችን ጋር ለችጋር ተዳርገናል ሲሉ ሠራተኞቹ አማረዋል።  ሠራተኞቹ ለአንድ ቀን በግቢው ውስጥ የረሀብ አድማ ቢያደርጉም ከሌሊቱ 6 ሠዓት ላይ በፖሊስ ኃይል እንዲወጡ ተደርገዋል። የሰራተኞቹ ማኅበር በበኩሉ ይህ ሕገወጥ ድርጊት እስካልተቀለበሰ ድረስ ወደ ቀጣይ ርምጃ እንሸጋገራለን ሲል ዝቷል። ከአዲስ አበባ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል።


ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ