1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሕዝብ እድገት ፍጥነት

ሐሙስ፣ ኅዳር 6 2005

የአፍሪቃ ህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ በመሄድ ላይ እንደሆነ ዘገባዎች እያመለከቱ ነዉ። የህዝብ ቁጥር እየጨመረ በሄደባቸዉ የአፍሪቃ ሀገሮችም የተፈጥሮ ሀብቶች ዉስኑንነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመሆኑ ረሃብና ድህነት ቀጣይ እጣ ፈንታ መሆናቸዉ ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/16k7c
ምስል Getty Images

የተመድ በጎርጎሮሳዊዉ የዘመን ቀመር 2050ዓ,ም አሁን ባለዉ የዓለም ህዝብ ቁጥር ላይ ተጨማሪ 117 ሚሊዩን እንደሚታከል ከወዲሁ ገምቷል። የቤተሰብ ምጣኔና የስነህዝብ ትምህርቶች ተስፋፍተዉ በየሀገራቱ በበቂ ሁኔታ ባለመዳረሳቸዉም ሰዎች ከሰብዓዊ መብቶቻቸዉ አንዱ የሆነዉን የመዉለድ ያለመዉለድ ዉሳኔ ተግባራዊ ማድረግ እንዳልቻሉ ትናንት ይፋ የሆነዉ የድርጅቱ የስነህዝብ ተቋም UNFPA ዘገባ አመልክቷል። በተለይም ያገቡም ሆኑ ያላገቡ ሴቶች የእርግዝና መከላከያ ስልቶችን ስለማያገኙ፤ ወይም ትምህርትና መረጃ ስላልተዳረ እንዲሁም እንቅፋት በሆኑባቸዉ የኤኮኖሚና ማኅበራዊ ጉዳዮች ምክንያት መብታቸዉን መጠቀም እንዳልቻሉም ዘገባዉ ገልጿል። ዘገባዉን ይፋ ያደረጉት የድርጅቱ ተወካይ ቬርነር ሃዉግ፤

Schwangere Frauen in Äthiopien
ምስል Getty Images

«ይህም ማለት የቤተሰባቸዉን ቁጥር መመጠን ከሚፈልጉ ከ15 እስከ 49 የእድሜ ክልል ከሚገኙ ሴቶች ከአራቱ አንዷ ይህን እድል አያገኙም ማለት ነዉ። ይም የራስ ቤተሰብን የመመጠን ዉሳኔ መብት ተቃራኒ ነዉ።»

ዘገባዎች እንደሚሉት ከሆነም በተለይ በአፍሪቃ የህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እያደገነዉ። በየሀገራቱ ካለዉ የተፈጥሮ ሀብት መመናመን አንፃር ሲታይም በክፍለ ዓለሙ የህዝብ ቁጥር እየጨመረ መሄዱ ረሃብና ድህነትን በቀጣይነት መጋበዙ አይቀሬ ነዉ። በዚህ ምክንያትም ለየሀገራቱ የሚሰጠዉ የልማት ርዳታ የቤተሰብ ምጣኔን ማገናዘብን እንዲያካትት ተጠይቋል።

የጀርመንየኤኮኖሚናየልማትትብብርሚኒስትርድሪክኒብልስለቤተሰብ ምጣኔ ሲታሰብ ታዳጊ ሴቶች የተለየ ትኩረት ሊደረግላቸዉ ይገባል ባይ ናቸዉ፤

«በዚህ ጉዳይ ላይ እያንዳንዷ ታዳጊ ወጣት የተለየ ትኩረት ያስፈልጋታል። ምክንያቱም ካልተፈለገ ርግዝና ራሷን እንድትከላከል አማራጮቹ ሊኖሯት ይገባልና። ይህ ደግሞ ራስ የመወሰን ጥያቄ ብቻም አይደለም፤ ይልቁንም ወጣቷ ቀሪ ህይወቷን ከድህነት ነፃ ሆና መኖር የምትችልበትን መንገድ ያመቻቻል።»

7 Milliarden Menschen auf der Erde Flash-Galerie
ምስል picture-alliance/dpa

እንደዘገባዉ አፍሪቃዉስጥበአማካኝአንዲትእናትአምስትልጆችንወደዚችምድርታመጣለች።አዳጊ ሀገሮች ዉስጥ ስለቤተሰብ ምጣኔና የወሊድ ቁጥጥር ተገቢዉን የምክር አገልግሎት ለሴቶች ለማዳረስ 8 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ያስፈልጋል። ለጊዜ አሁን ያለዉ የዚህን መጠን ግማሽ ያህሉ መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ። አገልግሎቱንም ሆነ ትምህርቱን ለማዳረስ ካለዉ የገንዘብ እጥረት በተጨማሪም ሌላ እንቅፋቶች መኖራቸዉን የUNFPAዉ ቫርነር ሃዉግ ያመለክታሉ፤

«የመንግስታት በቂ የፖለቲካ ድጋፍ አለመስጠት። ያገቡ ሴቶች የእርግዝና መከላከያ መጠቀማቸዉን የሚያከላክሉ አለያም የሚያግዱ ባህላዊና ሃይማኖታዊ እንቅፋቶች መኖራቸዉ ሌላዉ ችግር ነዉ።»

የህዝብ ቁጥርን ለመመጠን እንዲቻልም በተለይ የአፍሪቃ፤ ላቲን አሜሪካ እስያ መንግስታት ኅብረተሰቡ ኮንዶም እንዲጠቀም ግድ እንዲሉም የዓለም ህዝብ ቁጥርን ያመለከተዉ ዘገባ ይቋል። ፅንስን የማጨናገፍ ተግባርን ለመግታት የእርግዝና መከላከያን መጠቀም የተሻለ መሆኑን ያመለከተዉ የጀርመን የስነህዝብ ተቋም ከአዉሮጳዉያኑ 1960 እስከ 2000ዓ,ም ድረስ መከላከያ የሚጠቀሙ ወገኖች ቁጥር ከ10 ወደ 50 በመቶ ከፍ ብሎ እንደነበር ጠቁሟል። ሆኖማ ባለፉ አስር ዓመት ግን የተለወጠ ነገር አለመኖሩ ነዉ ያመለከተዉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ