1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሕፃናት ጤናና ህክምናዉ በኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ ጥር 14 2005

በየዓመቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ ወደሶስት ሚሊዮን ሕፃናት እንደሚወለዱ ይገመታል። በተቃራኒዉ በዓመት ከመቶ ሺህ በላይ ሕፃናት በተለያዩ የጤና እክሎች ህይወታቸዉ ያልፋል። ሀገሪቱ ያሏት የሕጻናት ሃኪሞች ቁጥር ደግሞ አራት መቶ አይሞላም።

https://p.dw.com/p/17PVk
ምስል AP Photo

ለሕፃናት የህክምና አገልግሎት መስጫ ተቋማትና አገልግሎቱም የሕፃናትን ህይወት የሚቀጥፎ በሽታዎችን ለመከላከል በተለይ በገጠር አሳሳቢነቱ አሁንም እንዳለ ነዉ።

ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚወለዱ ሕፃናትን በተለይ ደግሞ ከአምስት ዓመት ዕድሜ በታች የሆኑትን በከፍተኛ ደረጃ ከሚያጠቁ በሽታዎች ተቅማጥ፤ ኩፍኝና ወባ አልፈዉ ተርፈዉ የብዙዎችን ህይወት በመቅጠፍ ይጠቀሳሉ።

በተለይ ደግሞ የሕፃናት ሃኪምና የዚሁ ዘርፍ ህክምና መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ቦጋለ ወርቁ ዋነኛዉ የሳንባ ምች መሆኑን ይገልፃሉ።

በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህፃናት የሚወለዱባት ሀገር ኢትዮጵያ ያሏት የሕፃናት ሃኪሞች ቁጥርና የህክምና ይዞታዉ እንዴት ነዉ ባለሙያዉን አነጋግረናል። ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ